ጥራት ያለው ኮረሪማ ለገበያ ለማቅረብና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ትኩረት መደረጉን የአሪ ዞን ቡናና ቅመማቅመም ጽህፈት ቤት አስታወቀ
በበጀት አመቱ ዞኑ ከ15 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በኮረሪማ መሸፈኑንም ገልጿል።
በዞኑ በኮረሪማ ምርት የተሰማሩ የሰሜን አሪ እና ዎባ አሪ ወረዳ አርሶአደሮች ከዘርፉ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የምርቱን ጥራት የሚቀንሱ ተግባራትን ለመግታት በጋራ መሥራት እንደሚያስፈልግ በኮረሪማ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች ገልጸዋል።
ጥራት ያለው ኮረሪማን ለዓለም ገበያ ለማቅረብና የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለመጨመር ትኩረት መደረጉን በዞኑ የሰሜን ኣሪ እና የዎባ አሪ ወረዳ አስተዳዳሪዎች ገልፀዋል።
የኣሪ ዞን የቡናና ቅመማቅመም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ርብቃ እሳቱ፤ ጥራት ያለውን ኮረሪማ ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ትኩረት መደረጉን ገልፀው፤ በዞኑ 15 ሺህ ሄክታር መሬት በኮረሪማ መሸፈኑን አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል