ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምዕመናን ክልል አቀፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ የካቲት 30/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት ”በመደመር መንግስት እይታ የኃይማኖት ተቋማት ሚና” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምዕመናን ክልል አቀፍ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ እና የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ግለሰቦች እየተሳተፉ ይገኛል።
ዘጋቢ: ኤደን ተረፈ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ