የሙስሊሙ ማህበረሰብ በረመዳን ጾም ወቅት የሀይማኖቱ አስተምህሮ የሆነውን በጎ ተግባራት በማከናወን ማሳለፍ እንደሚገባ ተገለጸ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዲላ ከተማ አስተዳዳር የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ኡስታዝ አብድረህማን አብድቁ፥ በረመዳን ጾም ወቅት ሀይማኖታዊ ስርዓቶችንና እሴቶችን መተግበር ተገቢ መሆኑን አስታውቀዋል።
ኡስታዝ አብድረህማን የረመዳን ጾም የእስልምና እምነት ተከታዮች በእምነቱ ካሉት መሠረታዊ መርሆች አንዱ መሆኑን ጠቁመው፥ ጾሙ ለእምነቱ ተከታዮች የተቸገሩትን የመርዳት ጥበብ በመሆኑ፥ ለጤንነት፣ በስነ-ምግባር ለመታነፅ፣ ብሎም ከአላስፈላጊ ተግባራት እንድንጠነቀቅ የሚያደርግ እንደሆነና የተቸገሩትን በመርዳት በጎነትን በመተግበር ማሳለፍ የሀይማኖቱ አስተምህሮ መሆኑን ኡስታዙ አብራርተዋል።
በሙስሊም እምነት ተከታዮች ዘንድ በረመዳን ጾም ወቅት የመረዳዳት በጎ ተግባራትና የመልካምነት እሴት ጎልቶ የሚታይበት በመሆኑ በዚህ ጾም ወቅት በሀይማኖታዊ ስርዓት “ዘካ” የሚወጣበት መሆኑን አመላክተው፥ “ዘካ” ማለት ትርጉሙ መፋፋት ሲሆን ለድሆች ሀቅ በመክፈል ሀብታችን እንዲፋፋ በማድረግ ለሚገባቸው ሰዎች የሚሰጥ መስዋወት ነው ሲሉም ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል።
በቀጣይ ሁሉንም ባሳተፈ መልኩ የመረዳዳት እሴቱን አጠንክሮ ለመቀጠል የዘካ አወጣጥ ስርዓታችንን ጠቅላይ የእስልምና ጉዳዮች የሚያወርደውን አሰራር አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
የቀሩት ቀናት እጅግ ወሳኝ የጾም ወቅት በመሆኑ የእስልምና አስተምህሮት ስርዐትን በመተግበር የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል
ዘጋቢ: ፅጌ ደምሴ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ባለፉት ዘጠኝ ወራት 5.5 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በተለያዩ ዘርፎች ወደስራ መግባታቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ
በዳዉሮ ዞን እየተሠሩ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ለህዝቡ የመልማት ጥያቄ ምላሽ እያስገኙ መሆናቸዉ ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ
በዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ዘርፍ በመሰማራታቸው የቤት ፍጆታን ከማሟላት ባሻገር በኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን በጋሞ ዞን ገረሴ ከተማ በዘርፉ የተሰማሩ አንዳንድ አካላት አረጋገጡ