የእምነት ተቋማት ለአገረ መንግስት ግንባታ ቁልፍ ሚና ያላቸው በመሆኑ ለሀገር ብልጽግና ኃይል አድርጎ መጠቀም እንደሚገባ ተመላከተ
ሀዋሳ፡ የካቲት 30/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) “የመደመር መንግስት ለሀይማኖት ተቋማት እኩልነትና ሰላም ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ከኣሪ ዞን ሁሉም ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የሀይማኖት ተቋማት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመደመር መንግስትና የሀይማኖት ተቋማት መካከል ያሉ ልዩነትቶችና የግንኙነት መርሆዎች ላይ ያተኮረው የምክክር መድረክ በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ የተለያዩ አዳራሾች እየተካሄደ ነው።
በመድረኮቹ እንደ ሀይማኖት ተቋማቱ ባህሪያት የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተካሄ ነው።
“የመደመር መንግስት ለሀይማኖት ተቋማት እኩልነትና ሰላም ግንባታችን” በሚል መርህ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ ከኣሪ ዞን ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች የተውጣጡ የሁሉም የሀይማኖት ተቋቋማት አመራሮችና ተወካዮቻቸው እየተሳተፉበት ይገኛል።
ዘጋቢ: ወንድሜነህ አድማሱ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ከ20 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በኮረሪማ ምርት እየለማ መሆኑ ተገለጸ
በጎፋ ዞን ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች ክልላዊ የ6ኛ ክፍል ፈተና እየተሰጠ ነው
የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች በመመለስ በኩል ከመንግስት ጥረት ባለፈ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና የጎላ መሆኑን የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ ተናገሩ