ሀዋሳ፡ የካቲት 30/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ብልፅግና እንዲረጋገጥ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አበርክታለች ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር እና የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አበባዬሁ ታደሰ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
”የመደመር መንግስት እና የሀይማኖት ተቋማት” በሚል መሪ ቃል ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በአርባምንጭ እየተካሄደ ነው።
በመርሀ-ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ(ዶ/ር)፥ የምክክር መድረኩ በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ተግባቦት በመፍጠር ሀገራዊ ሰላምን የማጽናትና አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት በማሰብ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር እና የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አበባዬሁ ታደሰ(ዶ/ር)፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ አገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ ትልቅ ሚና የተጫወተች፣ ሰብአዊነትን፣ ባህልን፣ ቅርስንና ማንነትን ለዛሬው ትውልድ ያሸጋገረች ናት ሲሉ ገልጸዋል።
ዶ/ር አበባዬሁ ታደሰ አክለውም፥ የታሪክና የቅርስ ማዕከል የሆነችውና ይህንንም ለሀገር ያበረከተችው ቤተክርስቲያኗ፥ ዛሬም ድረስ በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ የአገሪቱ ብልፅግና እንዲረጋገጥ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አበርክታለች፣ እያበረከተች ትገኛለች ብለዋል።
አሁን አሁን በቤተክርስቲያን የተለያዩ አጀንዳዎችን ይዘው ህዝብን ለመከፋፈል የሚጥሩ አካላትን እና በሃይማኖት ሽፋን አድርገው ሀገርን የሚያውኩ አካላትን ኃላፊነትን በመውሰድ የእርምት ስራዎችን መስራት ከሁሉም ይጠበቃል ሲሉ አብራርተዋል ።
በመድረኩ “የመደመር መንግስት እና የሀይማኖት ተቋማት” የሚልና የሀይማኖት ተቋማት ለሰላም እንዲሁም ለአንድነት ባላቸው ሚና ዙሪያ የውይይት ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።
በመርሀ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር እና የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አበባዬሁ ታደሰ(ዶ/ር)፣ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ(ዶ/ር)፣ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሽመልስ ታደሰ፣ የጋሞ ጎፋና የባስኬቶ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የሲኖዶስ አባል ብፁህ አቡነ ኤልያስን ጨምሮ በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች የተወጣጡ አባቶችና ምዕመናን እየተሳተፉ ይገኛሉ ።
ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ብልፅግና እንዲረጋገጥ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማበርከቷ ተገለጸ

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ