ሪያል ማድሪድ ማንቸስተር ሲቲን በደርሶ መልስ አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ

ሪያል ማድሪድ ማንቸስተር ሲቲን በደርሶ መልስ አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ማንቸስተር ሲቲን በደርሶ መልስ አሸንፎ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል።

ክሊያን ምባፔ ደምቆ ባመሸበት የመልስ ጨዋታ ሎስብላንኮዎቹ በቤርናቢዩ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

ሦስቱንም የሪያል ማድሪድ የማሸነፊያ ግቦች ክሊያን ምባፔ በማስቆጠር ሃትሪክ ሰርቷል።

ኒኮ ጎንዛሌዝ በማንቸስተር ማልያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስቆጠራት ጎል ማስተዛዘኛ ከመሆን በዘለለ ሌላ ፋይዳ ሳይኖራት ቀርቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ ማንቸስተር ሲቲን በድምር ውጤት 6ለ3 በማሸነፍ ወደ 16 ውስጥ ማለፉን አረጋግጧል።

የ26 ዓመቱ ተጫዋች ክሊያን ምባፔ በተጫዋችነት ዘመኑ 501ኛው የጎል ተሳተፎ አከናውኗል።

በሌሎች የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር ያካሄዱት ጨዋታ ያለጎል በአቻ ውጤት ቢጠናቀቅም ዶርትሙንድ በድምር ውጤት 3ለ0 አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

ፒኤስጂ ብረስትን በድምር ውጤት 10ለ0 በማሸነፍ ወደ 16 ውስጥ አልፏል።

ዩቨንቱስ ግን በሆላንዱ ክለብ ፒኤስቪ ኤይንድሆቨን በድምር ውጤት 4ለ3 ተሸንፎ ወደ ቀጣዩ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

በሙሉቀን ባሳ