ህዝቡ የሚያነሳቸውን የፍትህ ጥያቄዎች በአግባቡ ከመመለስ አኳያ የፍትህ ተቋማት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አሳሰቡ
የወላይታ ዞን ፍትህ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ሴክቶሪያል ጉባኤ ተካሂዷል።
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ፤ የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መፍታት የሚቻለው ትክክለኛ የፍትህ ስርዓት ማስፈን ሲቻል ነው ብለዋል።
የዜጎችን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ በተለይም የፍትህ ተቋማት በህዝቡ ዘንድ አመኔታ መፍጠር የሚችሉ ትክክለኛ ፍትህ ለማረጋገጥ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ዜጎች የህግ የበላይነትን ጠንቅቀው እንዲያውቁ ከፍትህ ተቋማት በኩል የተጠናከረ ሥራ መሰራት አለበት ያሉት ዋና አስተዳዳሪ፤ ህብረተሰቡ ወንጀልን ቀድሞ ከመከላከል አኳያ የግንዛቤ ሥራዎች ላይ መሰራት አለበት ብለዋል።
በዞኑ የህዝቡን ሠላም ለመጠበቅና የተሻለ የፍትህ ሥርዓት በመዘርጋት የዜጎችን ጥያቄ ለመመለስ በተደረገው ጥረት ባለፉት ስድስት ወራት አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል።
ህዝቡን በፍትህ አገልግሎት ለማርካት የፍትህ ሥርዓት የማዘመን ስራ በቁርጠኝነት መሰራት አለበት በማለት በየደረጃው ያሉ የፍትህ ተቋማትም ሀላፊነታቸውን በትጋት መወጣት አለባቸው ብለዋል።
የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋው ስምኦን በዞኑ የህብረተሰቡን ፍትህ ጥያቄዎችን ለመመለስ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይም ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና እንደጉድለት የታዩ ክፍተቶችን ለማረም በቅንጅት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
ከመማር ማስተማር ተግባር ባለፈ የአካባቢ ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የሚዛን ግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ አስታወቀ
የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ(ዶ/ር) መጭው ጊዜ ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ብርሃን የምንሸጋገርበት ብሩህ ዘመን መሆኑን ተናገሩ
በተቀሩት አጭር ቀናት ህብረተሠቡ የመራጭነት ካርዱን በመውሰድ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳና አካባቢው የፌደራልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቀረቡ