ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ማካሔድ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተገለፀ
በጌዴኦ ዞን በተለያዩ ባህላዊ ጫዋታዎችና ዘመናዊ ስፖርት ሻምፒዮና ውድድር እየተካሄደ ነው፡፡
በውድድሩ ለክልሉ ሻምፒዮና የሚሳተፉ ስፖርተኞችን ከመምረጥ ባለፈ በቡድን ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ተተኪዎችን ለማፍራት እየተሠራ መሆኑን የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ምስጋና በቀለ ተናግረዋል፡፡
በሁሉም ስፖርት ዓይነቶች በዞኑ ካሉ መዋቅሮች የተወከሉ የተለያዩ ስፖርተኞች መሳተፋቸውን የገለጹት ኃላፊዋ፥ እንደነዚህ ዓይነት ጨዋታዎች መዘጋጀታቸው የህዝብ ለሕዝብ ትስስር ለማጠናከርና ሰላምን ለማስፈን ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በልዩ ልዩ ስፖርት የተሳተፉ ወጣቶች የሻምፒዮና መዘጋጀት አቅማቸውን እንዲያሳዩና ልምድ እንዲቀስሙ በር ከፋች መሆኑን ጠቀሰዋል፡፡
የይርጋጨፌ የሴቶች ክለብ አሰልጣኝ ቢንያም በቀለ በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ብቁና ውጤታማ ተጫዋቾችን ለማግኘት መሰል ውድድሮች ጠቀሜታቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
ዘጋቢ: ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ሪያል ማድሪድ ማንቸስተር ሲቲን በደርሶ መልስ አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ
ሊቨርፑል ዎልቭስን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አትሌት ዩሚፍ ቀጀልቻ በ10 ኪሎ ሜትር የግሉን እና የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ