ሊዮኔል ሜሲ ወደ ባርሴሎና ለመመለስ ወሰነ
የስምንት ጊዜ የባሎንዲኦር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ በቀጣይ ወደ ልጅነት ክለቡ ባርሴሎና ለመመለስ መወሰኑ ተዘግቧል።
አርጄንቲናዊው ኮከብ መቼ እንደሚመለስ እና በምን ሚና ክለቡን እንደሚቀላቀል አለመገለፁን ማርካ አስነብቧል።
የቀድሞ የባርሴሎና ታሪካዊው ተጫዋች ከወራት በፊት ካምፕኑ ስታዲየምን በሚስጥር ከጎበኘ በኋላ ወደ ካታላኑ ክለብ ተመልሶ የመምጣት ተስፋ እንዳለው መግለፁ ይታወሳል።
ሊዮኔል ሜሲ በስፔንም ሆነ በዓለም ካሉ ክለቦች ስመ ገናና ከሆኑ ክለቦች አንዱ ከሆነው ባርሴሎና ጋር በፈረንጆቹ 2021 ላይ መለያየቱ ይታወሳል።
በአሁን ሰዓት በአሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ እየተጫወተ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ከማክስ ዶውማን ጋር መስራት ትልቅ ደስታ ነው” ሚኬል አርቴታ
ስፖርት ፍቅርን፣ ሰላምን እና አንድነትን ለማምጣት ወሳኝ ነው – የቡርጂ ዞን አስተዳደር
“እናቴ ሆይ ደውይልኝ!”