ጥራት ያለው፣ ወቅታዊና ተደራሽ የሆነ መረጃ ለህብረተሰቡ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለማድረስ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚዛን ቅርንጫፍ ጣቢያ አስታወቀ
ጣቢያው የተቋሙን የስድስት ወራት አፈጻጸም ገምግሟል።
በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ስር ከሚተዳደሩት አንዱ የሆነው የሚዛን ቅርንጫፍ ጣቢያ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በሚገኙ ሁለት ዞኖች አማርኛ ቋንቋን ጨምሮ በአምስት የብሔረሰብ ቋንቋዎች አስተማሪ፣ አዝናኝና አሳዋቂ የሆኑ ዜናና ፕሮግራሞችን በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥንና በማህበራዊ ሚዲያ መረጃ ለህብረተሰቡ በማድረስ ላይ ይገኛል።
በተለይም በህብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እንዲያገኙ ከማድረግ አንጻር ተቋሙ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
ተቋሙ የስድስት ወራት አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት የተቋሙ ስራ አስኪያጅ አቶ ትእዛዙ ኪንጫ፤ ተቋሙ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ ለህብረተሰቡ በማድረስ በኩል የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
በአፈፃፀም ሂደት የተገኙ ጥንካሬዎችን በማጠናከር ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ ስድስት ወራት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ መዘጋጀት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የተቋሙ ባለሙያዎች በበኩላቸው ተቋሙ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ጭምር በማሰራጨት ህብረተሰቡን የመረጃ ተጠቃሚ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው የገበያ ልማት ስራዎችን በማጠናከር በጋራ የገቢ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ዘጋቢ: አብዮት በቀለ – ከሚዛን ጣቢያችን

More Stories
የግል እና የጋራ መጸዳጃ ቤቶችን በተገቢው በመጠቀም ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስገነዘበ
12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በተቋማት የድርጊት መርሐ-ግብርና በፀደቀላቸው በጀት መሠረት ማሰራጨቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ አስታወቀ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ አስተዳደር እየተገነባ የሚገኘውን ብሉ ኤለፋንት ፋይበር ቦርድ ካምፓኒ ጎበኙ