አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉይ መልቀቂያ አስገቡ
የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድነሰ ዋና አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉይ በገዛ ፈቃዳቸው ከሀላፊነት ለመነሳት መልቀቂያ ማስገባታቸው ተገልጿል።
አሰልጣኙ ላስገቡት የስራ መልቀቂያ የሞሮኮ እግርኳስ ፌዴሬሽን እስካሁን ምንም የገለፀው ነገር እንደሌለ ፉት መርካቶ አስነብቧል።
የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ በፈረንጆቹ 2022 ነበር ብሔራዊ ቡድኑን በሀላፊነት የተረከቡት።
በቆይታቸውም ሞሮኮን በዓለም ዋንጫው ታሪክ ለግማሽ ፍፃሜ መድረስ የቻለች የመጀመሪያው አፍሪካዊት ሀገር እንድትሆን አስችለዋታል።
በተጨማሪም ከአንድ ወር በፊት በተጠናቀቀው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቡድኑን ከ21 ዓመታት በኋላ ለፍፃሜ ማብቃታቸው ይታወሳል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ከማክስ ዶውማን ጋር መስራት ትልቅ ደስታ ነው” ሚኬል አርቴታ
ስፖርት ፍቅርን፣ ሰላምን እና አንድነትን ለማምጣት ወሳኝ ነው – የቡርጂ ዞን አስተዳደር
“እናቴ ሆይ ደውይልኝ!”