በወረዳው አሞገራ ቀበሌ ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ የሆነው የኧቢጥሪ መንደር ምረቃ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የእኖር ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ቃሲም ጸጋዬ እንደተናገሩት፤ ጥራት ያላቸው የግል እና የጋራ መጸዳጃ ቤቶችን በመገንባትና በተገቢው በመጠቀም ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን አስቀድሞ መከላከል ይገባል።
በወረዳው ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ጽዱ መንደርን ለመፍጠር በርካታ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑንና ከጊዜ ወደ ጊዜም ለውጦች እየታዩ መሆኑን ተናግረዋል።
በወረዳው አሞገራ ቀበሌ ኧቢጥሪ መንደር ከሜዳ መጸዳዳት የጸዳ ሆኖ እንዲመረቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም አቶ ቃሲም ምስጋናቸውንም አቅርበዋል።
መርሀግብሩ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ የሃይጅንና ሳኒቴሽን ባለሙያ አቶ ሳምሶን ተስፋዬ፤ በዞኑ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ህብረተሰቡ የግልና የአካባቢውን ንጽህና በመጠበቅ ጤናማና አምራች ዜጋ እንዲፈጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የድጋፍና ክትትል ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል።
በወረዳው አሞገራ ቀበሌ ኧቢጥሪ መንደር የተከናወነው ጽዱ መንደር የመፍጠር ተግባር ለሌሎችም አስተማሪ ነው ብለዋል።
የአሞገራ ቀበሌ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ ወ/ሮ አልማዝ ጸጋዬ በቀበሌያቸው የሚገኙ መንደሮችን ጽዱና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን በኧቢጥሪ መንደር ያሉትን አደረጃጀቶች በመጠቀምና ለህብረተሰቡ አስፈላጊው ግንዛቤ ተፈጥሮለት በተሰሩ ስራዎች ከሜዳ መጸዳዳት ነጻ ሆኖ ሊመረቅ ችሏል ብለዋል።
የመንደሩ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ተዋበች ጨሩና ጀሚላ ኡመር በጋራ በሰጡት አስተያየት፤ በቀበሌው የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክረ ሃሳብ በተገቢው ተጠቅመው የራሳቸውና የቤተሰባቸው ጤና የተጠበቀ እንዲሆን የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል።
በዕለቱ ከጽዱ መንደር ጋር ተያያዥ የሆኑ ተግባራትን አስመልክቶ የመስክ ጉብኝት ተደርጓል፡፡
ዘጋቢ፡ ፉአድ አብደላ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
የግል እና የጋራ መጸዳጃ ቤቶችን በተገቢው በመጠቀም ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስገነዘበ

More Stories
12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በተቋማት የድርጊት መርሐ-ግብርና በፀደቀላቸው በጀት መሠረት ማሰራጨቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ አስታወቀ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ አስተዳደር እየተገነባ የሚገኘውን ብሉ ኤለፋንት ፋይበር ቦርድ ካምፓኒ ጎበኙ
በቀቤና ልዩ ወረዳ የሚገነቡት የኢማም ሀሰን ኡንጀሞ ሆስፒታል እና የፈትሁዲን ላሉተ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች የማህበረሰቡን የዘመናት የልማት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ መሆናቸውን ተገለፀ