የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተላቸውን ተቋማት የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ
ሀዋሳ: ጥር 28/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተላቸውን ተቋማት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ማድመጥ ጀምሯል።
የክልሉ ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ግብርና ቢሮ፣ ባህልና ቱሪዝም ፣ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ፣ የደንና አከባቢ ጥበቃ ቢሮ የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ይገመግማል ተብሎ ይጠበቃል።
በክልሉ የአርብቶ አደር አካባቢዎች በ2017 መጀመሪያ ግማሽ አመት የተከናወኑ ጠንካራ የልማት የመልካም አስተዳደር ስኬቶች በሪፖርቱ የተመላከተ ሲሆን፥ የግብርናና ገጠር ልማት ቋሚ ኮሚቴ በቀረበው ሪፖርት ላይ ጥያቄዎችንና ግብረ መልሶችን እየሰጠ ነው።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጠንክር ጠንካ ጨምሮ የቋሚ ኮሚቴ አባላትና የተቋማቱ የቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም የማኔጅመንት አባላት እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ
More Stories
የሰንበት ገበያ ማዕከል ሸማቹና አምራቹ ማህበረሰብ በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የላቀ ሚና እንዳለው ተገለጸ
በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ከ36 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ የተሰራው የኡማ ባኬ መንገድ ተጠናቆ ተመረቀ
የ2017 የክረምት ወራት የገቢ አሰባሰብና የ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ምዝገባና እድሳት ስራ በአግባቡ ለመስራት መዘጋጀታቸውን በጋሞ ዞን ባለድርሻ አካላት ገለጹ