በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የአርባ ምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፣ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን አርባ ምንጭ ቅርንጫፍ በጋራ በመሆን ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረጉ
ተቋማቱ በአደጋው ምክንያት ሕይወታቸውን ባጡና ጉዳት በደረሰባቸው ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል።
በጋራ ያሰባሰቡት አልባሳትና የምግብ ግብዓቶች “የወገን ለወገን ደራሽነት” ማሳያ መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህ አሁን የተደረገው ድጋፍ የመጀመሪያ ዙር መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተቋማቱ የበኩላቸውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ተስፉጽዮን ዘነበ በበኩላቸው ተቋማቱ ላደረጉት ድጋፍ በዞኑ አስተዳደርና በተጎጂዎች ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ ፡ ተመኙህ ገረሱ-ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ