‎የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በጋሞ ዞን የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

‎የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በጋሞ ዞን የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
‎
‎ሀዋሳ፡ መጋቢት 09/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በጋሞ ዞን የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 500ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።
‎
‎የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ዋና እምባ ጠባቂ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደ ሀገር የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው፥ የ500ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ለአደጋው ተጎጂዎች ማድረጉን ተናግረዋል።
‎
‎ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት፥ በቀጣይም ከአደጋው የተረፉ ወገኖች ተገቢው ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አመላክተዋል።
‎
‎ተቋሙም በሚደረጉ ድጋፎች የበኩሉን እንደሚወጣ ገልፀዋል።
‎
‎የጋሞ ሀገር ሽማግሌ ተቋሙ ላደረገው ድጋፍና ላሳየው አለኝታነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዘጋቢ፡ ብዙነሽ ዘውዱ