ሌላኛዋ አስተማማኝ አጋር
ሁኔታው ከጊዜ ቀደ ጊዜ እያደገ ካለው የአፍሪካ ተስፋ ጋር ብቻ የተያያዘ አይደለም። ደጅ ላይ ቆመው በተቸገረች ጊዜ ሁሉ ከሚደርሱላት የወዳጆች ፍላጎት ጭምር እንጂ፡፡ አንዳንድ ሀገራት ከደጋፊነት ወደ ቁልፍ አጋርነት መሸጋገራቸው ለፍላጎቶቿ መሳካት ልዩ ዕድል ፈጥሯል፡፡
ሀገሪቱ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ነች። ችግር በደረሰና ፈተናው በበዛበት ጊዜ ሁሉ ፈጥኖ ደራሽ የሆነችው ሀገር እንደ ቻይናና ቱርክ ካሉ ቋሚ ወዳጆች ጋርም ትመሳሰላለች። በተለይ ሀገራችን በችግር ውስጥ በገባችበት ጊዜ ያደረገችው ድጋፍ መቼም ከኢትዮጵያዊያን አዕምሮ የሚጠፋ አይደለም፡፡
ሰሞኑን የወጣው መረጃም አጋርነቷን በማሳየት የአፍሪካዊያን ተጨማሪ ተስፋ መሆንዋን አብስሯል፡፡ የአፍሪካ ግንባር ቀደም አልሚ በመሆን በታዳሽ ኃይልና በመሠረተ-ልማት የምታስመዘግበው ተስፋም ተገልጿል፡፡
“የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የአፍሪካ ዋነኛ አልሚ በመሆን የምትጫወተውን ሚና አጠናክራለች” በሚለው ርዕስ ሥር አፍሪካ ኒውስ ሰሞኑን ያወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተውም ሚናዋን አሳድጋ በተለይ ታዳሽ ኃይል በመሳሰሉ ዘርፎች እየሠራች ትገኛለች፡፡
በሰሜን አፍሪካ ካሉ የጸኃይ ኃይል ፕሮጀክቶች ጀምሮ ትላልቅ ሥራዎችን እንዳከናወነች ያስታወቀው ዘገባው የአህጉሪቱን ሥነ-ምህዳር እየቀየረች መሆኑን ገልጿል ምንም እንኳን ከሠራተኛ ሥምሪትና አካባቢ ተጽዕኖ አንጻር ሥጋቶች ባይጠፉም፡፡
እየተከናወነ ያለው አስደማሚ ሥራ የምሁራንን ትኩረትም የሳበ ሲሆን የአረብ የኃይል ክለብ ፕሬዝዳንት የሆኑት ካሮል ናክዌ እንዲህ በማለት ገልጸውታል ቃለ-መጠይቅ በተደረገላቸው ጊዜ፡፡ ሀገሪቱን ከሌሎች ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች ወይም አልሚዎች ጋር በማነጻጸር ሲገልጹም ለየት ባለ ስትራቴጂክ ዕይታ እና በገንዘብ ኃይል መመራቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ የአፍሪካ መሪዎች ሚና ምን መሆን አለበት በማለትም ሀሳባቸውን ሲቀጥሉ ግንባር ቀደም ሚና በመጫወት አነዚህ ፕሮጀክቶች የተፈለገውን ተጨባጭ ውጤት ማምጣታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባቸው ጠቁመው ለዜጎቻቸውም የተሻለ ዕድል መፍጠር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ብልሃት ትክክለኛውን መንገድ መከተል እንደሆነ አሳስበው የአህጉሪቱ ፖሊሲ አውጪዎችም በትጋት መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ አካባቢያዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው ተናግረው በንጽጽር የውጭ ኢንቨስትመንት ማበረታታት እንዳለባቸውም አመልክተዋል፡፡
ከዚህ ዘገባ ወጣ ባለ መንገድ የተነሳው ሌላው ነገር ከሌሎች ጋር ተመሳስለው የሚገቡ ምርቶች መጠን መጨመር ሲሆን በአህጉሪቱ ይህንን በመዋጋት ረገድ ተጠቃሽ የሆነችው ሀገር ደግሞ ዚምባብዌ ነች፡፡ የእነዚህ ምርቶች ተጽዕኖ ምንድነው ተብሎ ሲጠየቅም ልክ እንደ ኮንትሮባንድ በህጋዊ አምራቸቾች ላይ እንቅፋት ሲፈጥር እንደ ማህበረሰብ ጤና ባሉ አገልግሎቶች ላይም ጉዳት እንደሚያስከትሉ ተገልጿል፡፡
ችግሩ ተመሳስለው ከተሠሩ የህክምና መገልገያዎች ጀምሮ በውሸት እስከተሠሩ ምግብ ዓይነቶች ሲደርስ መጠኑም በአሳሳቢ መልክ ማደጉ ነው የተገለጸው፡፡
ጉዳቱን ለመቀነስ ሲባል የሀገሪቱ ጉሙሩክ ባለሥልጣን ክትትልና ቁጥጥር ሥራውን እንዳጠናከረ ሲገለጽ ለዚህም ጠንካራ የድንበር ጥበቃ እና የህብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደግ ሥራዎች ተግባራዊ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡
መንግሥት ሸማች ማህበረሰቡን ለመጠበቅና ገበያውን ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ ስላለበት ሁኔታም ኪዝ ባፕቲስት የተባለው ጋዜጠኛ ገልጿል ያሉ ድክመቶችን ሁሉ በመጠቆም። ቁጥጥሩን ለማከናወን አስፈላጊ የሆነ ሀብት ያለመኖሩንንና ተመሳስለው የተሠሩ ምርቶች ጥራት መውረዱን በመግለጽ፡፡
የመንግሥት አመራሮች የችግሩን የረጅም ጊዜ ተጽዕኖ እና ማህበራዊ ጫና በመረዳት ያለሰለሰ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውንም ጠቅሷል፡፡
የመረጃ ምንጫችን አያይዞ ያወጣው ሌላ መልካም ዜና የአህጉሪቱ ምጣኔ ሀብት እያሳየ ያለው የማገገም አዝማሚያ ሲሆን ይህም በየጊዜው በሚወጣው የአፍሪካ ምጣኔ ሀብት አውትሉክ በተባለው ሪፖርት ተገልጿል፡፡
እስካሁን እንቅፋት ሆነው ከቆዩ ችግሮች ማለትም ከዋጋ ግሽበት፣ ከዕዳ ጫና እና አየር ንብረት ለውጥ ጋር ሲተያይ መልካም የተባለው ይህ ተስፋ በአሀዛዊ ስሌት ሁሉ የተገለጸ ሲሆን ይህም በፈረንጆቹ የጊዜ ቀመር በ2024 ከነበረው 3 ነጥብ 4 በመቶ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ዘንድሮ 3 ነጥብ 7 በመቶ መባሉ ተስፋ የሚያለመልም ነው፡፡ እንደ ኬንያ፣ ናይጀሪያ እና ደቡብ አፍሪካ የመሳሰሉት ጠንካራ ምጣኔ ሀብት ያላቸው ሀገራትም ድጋፍ ማድረጋቸው ተመላክቷል፡፡
ይህ አንጻራዊ ዕድገት የመጣው እንዴት ነው ተብሎ ሲጠየቅም ምክንያቱን ከተወሰዱ ዋና ዋና መዋቅራዊ ማሻሻያዎች ጋር ያገናኘው አፍሪካ ኒውስ በዘርፎች የፈሰሰውን መዋዕለ-ነዋይ እና የሸቀጦች ዋጋ መሻሻልም አስተዋጽኦ እንዳደረገ አስቀምጧል፡፡
ይሁን እንጂ እነዚህ ተስፋዎች ቀጣይ በመሆናቸው ላይ ባለሙያዎች ጥርጣሬ አላቸው የወጣቶች የሥራ አጥነትት፣ የመሠረተ-ልማት እጥረትና የአየር ንብረት ለውጥ በመሳሰሉ ችግሮች ላይ ትኩረቱ ሊጠናከር እንደሚገባ ስለሚፈለግ፡፡
More Stories
አንድ ነገር ቢጎድልህም ሌላ ነገር ተሰጥቶሀል – ወጣት ቢኒያም በሪሶ
ችግር ፈቺ የሆኑ አለም አቀፍ የምርምር ጽሁፎች አሳትሜያለሁ – ወጣት ሱራፌል ሙስጠፋ
የክልሉ ስኬት ሌላው ማሳያ