ሲዳማ ቡና የውድድር ዓመቱን በድል ጀመረ

ሲዳማ ቡና የውድድር ዓመቱን በድል ጀመረ

በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 4ለ1 በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን በድል ጀምሯል።

ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሰመረ ሀፍታይ በ36ኛው ደቂቃ ጎል አስቆጥሮ ወልዋሎን መሪ ማድረግ ችሎ ነበር።

ሆኖም ግን በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመራው ሲዳማ ቡና በሁለተኛው አጋማሽ ጌታሁን ባፋ በራሱ ላይ፣ አበባየሁ ሀጂሶ፣ አስቻለው ሙሳ እና ተመስገን መንገሻ ኳስ እና መረብን አገናኝተውለት ጣፋጭ ድል አሳክተዋል።

በ2ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐግር ሲዳማ ቡና ከሀዋሳ ከተማ ጋር ሲጫወት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከፋሲል ከነማ ጋር የሚገናኝ ይሆናል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ