ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በወልቂጤ ከተማ ከ127 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን ሞዴል የማህበረሰብ ትምህርት ቤት የምረቃ ስነ-ስርዓት በመከናወን ላይ ነው
ሀዋሳ፡ ጥር 27/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በጉብሬ ክፍለ ከተማ ከ127 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን ሞዴል የማህበረሰብ ትምህርት ቤት (ከ1ኛ-8ኛ) የምረቃ ስነ-ስርዓት በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል፣ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድርን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ከፌደራል፣ ከክልል፣ ከዞንና ከከተማ አስተዳደር ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ፍስሃ ክፍሌ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል