በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ በሞዴል ሴት አርሶአደር ማሳ ላይ ያለው የሙዝ ምርት በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረጉ ተጠቆመ
በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ ላይ መሆናቸውን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገልጿል።
በጋሞ ዞን በተለያዩ የግብርና ዘርፍ የተሰማሩ አልሚ ባለሃብቶች በፈጠሩት የስራ እድል በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።
በዞኑ ምዕራብ አባያ ወረዳ ኡጋዮ ቀበሌ በአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ በመሰማራት ውጤታማ የሆኑት ወ/ሮ መሰለች ሻቻ፤ በኪራይ ባገኙት 16 ሄክታር መሬት ሙዝ እና ሌሎች አትክልቶችን በማምረት ከራሳቸው አልፈው ለ20 ቋሚና 30 ለሚበልጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠራቸውን ጠቁመዋል።
በ2015 በጀት ዓመት በማህበር የጀመሩትን የግብርና ስራ በግል ማስቀጠል መቻላቸውና በ2 አመት ውስጥም 20 ሚሊየን ብር ካፒታል በማንቀሳቀስ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል ወ/ሮ መሰለች።
ስራቸውን የበለጠ ለማስፋት የኢንቨስትመንት መሬት እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ምላሽ በመጠበቅ ላይ የሚገኙት ወ/ሮ መሰለች፤ ወደ ማሳ የሚያደርስ የመንገድ መሰረተ-ልማት እንዲዘረጋ ጠይቀዋል።
የምዕራብ አባያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወገኔ ዋሎ፤ የወረዳው አየር ንብረት በአትክልት እና ፍራፍሬ ዘርፍ ለሚሰማሩ አልሚ ባለሃብቶች ምቹ በመሆኑ አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍ እየሰጠን ነው ብለዋል።
የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻምበል ቦኩ፤ በዞኑ በአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ የግል ባለሃብቶች መኖራቸውን ጠቅሰው መምሪያው ሙያዊ እና የግብአት ድጋፍ በማድረግ እንጀሚያበረታታ አብራርተዋል።
የስራ እድል ከተፈጠረላቸው መካከል ወጣት ጌትነት ሻቻ እንዳስረዳው፤ በቋሚነት በሚያገኘው ወርሃዊ ገቢ ከራሱ አልፎ ቤተሰቡን ማስተዳደር መቻሉን መስክሯል።
ከቀበሌው ነዋሪዎች መካከል ወ/ሮ ናዝሬት አካሉ እና አቶ ጎሳዬ ሹራ እንዳስረዱት፤ በአካባቢው በግሉ ዘርፍ የተሰማሩ አልሚ ባለሃብቶች መበራከት ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለልምድ ልውውጥ ያለው አበርክቶ ከፍተኛ ነው።
ዘጋቢ፡ አሰግድ ተረፈ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የሀለባ ዞን ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ቢልዮን 293 ሚልዮን ብር ባለይ በጀት አጸደቀ
መስራት እየቻሉ የገንዘብ እጥረት የገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግሮች ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ቀላል አለመሆኑ ተገለጸ
በስልጤ ልማት ማህበር ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር የተሰበሰቡ የአካባቢው ተወላጆች በዞኑ በሚገኙ የላንፉሮ ወረዳና ጦራ ከተማ አስተዳደር ችግኞችን ተክለዋል ።