በስልጤ ልማት ማህበር ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር የተሰበሰቡ የአካባቢው ተወላጆች በዞኑ በሚገኙ የላንፉሮ ወረዳና ጦራ ከተማ አስተዳደር ችግኞችን ተክለዋል ።

በስልጤ ልማት ማህበር ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር የተሰበሰቡ የአካባቢው ተወላጆች በዞኑ በሚገኙ የላንፉሮ ወረዳና ጦራ ከተማ አስተዳደር ችግኞችን ተክለዋል ።

በየአመቱ በስልጤ ልማት ማህበር (ጉዞ ስልማ) በሚዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሲርሞሎ እንደገለፁት አረንጓዴ ልማት የደን ልማት ከማስፋፋት ባለፈ የፍራፍሬ ልማትን ለማሳደግ እንደሚረዳ ገልፀዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊና የገጠር ክላስተር አስተባባሪ አቶ ኡስማን ሱሩር ከማይበሉ ወደሚበሉ ተክሎች በተደረገው የአረንጓዴ ልማት የፍራፍሬ የቡናና የበርበሬ ችግኞችን መትከል የምግብ ዋስትናን  ከማረጋገጥ ባለፈ በገቢ ራስን ለማገዝ ያስችላል ብለዋል።

የስልጤ ልማት ማህበር ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የሆነው የአረንጓዴ ልማት ህብረተሰቡን ለልማት ከማነሳሳት ባለፈ የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዲጎለብት ማድረጉን የዞኑ አስተዳዳሪ ዘይኔ ቢልካ ተናግረዋል ።

የስልጤ ልማት ማህበር ከተመሰረተ ጀምሮ በርካታ ህብረተሰብ ተኮር ስራዎችን ያከናወነ ሲሆን በችግኝ ተከላና የአረንጓዴ ልማት ዙሪያ ስኬታማ መሆኑን የልማት ማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሸምሴ ኑሪ ገልፀዋል ።

የአከባቢው ተወላጆች በበኩላቸው የአረንጓዴ ልማት ችግኝ ተከላው የተሳካ እንደነበር ገልፀው በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ራሄል አሊ