ብሔራዊ መግባባት የሰፈነባትን ሀገር ለትውልድ ለማስረከብ ሀገራዊ ምክክሩ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ብሔራዊ መግባባት የሰፈነባትን ሀገር ለትውልድ ለማስረከብ ሀገራዊ ምክክር ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን የምዕራብ ኦሞ ዞን የጀሙ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ህብረተሰቡ አሁን ላይ እየተሰራጨ ባለው የሀሰት መረጃ ሳይሸበር ከምክክር ኮሚሽን የሚሰጡ መግለጫዎችና በመንግስት ሚድያ የሚተላለፉ መረጃዎችን ብቻ መውሰድ እንዳለባቸው ተመላክቷል።
እንደ ነዋሪዎቹ ገለፃ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የፖለቲካ ቅራኔዎችን በሃሳብ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ውይይት በማድረግ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው አጀንዳ ነው ብለዋል።
ለዚህም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች፣ የፌደራል ተቋማትና በውጭ ከሚኖሩ ዜጎች ጋር ምክክር እያደረገም ይገኛል።
ሀምሌ 8/2018 የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ዜጎችም ይህን ታሪካዊ ዕድል በመጠቀም ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ጠንካራ ሀገረ መንግስትና ሰላማዊ የፖለቲካ ባህል የመገንባት ኃላፊነት እንዳለባቸው እና ምክክሩም ለሀገራችን ኢትዮጵያ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ያነጋገርናቸው የጀሙ ከተማ ነዋሪዎች አስረድተዋል።
ምክክሩ ሀገራዊ ጉዳዮች ወደ ሌላ አጀንዳ ሳያመሩ እርስ በእርስ በመግባባት የሚፈቱበት መሳሪያ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፥ ምክክሩ የተዛባ ትርክት ከማረም ባሻገር የተከማቹ ችግሮችን በመግባባት ይፈታል ብለዋል።
አካታች የሆነ የምክክር ጉባኤ መካሄዱ ለወደፊት ሊፈጠር የሚችል የከፋ ግጭት ከወዲሁ በማስቀረት የተጀመረውን አገራዊ ልማት ለማስቀጠል ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልፀው፥ ሀገራዊ ምክክር የቆዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ትልቅ መሣሪያ ነው መሆኑን ጠቁመው፥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት ከመንግስት ጎን በመቆም ሀገራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን ዳጉሳ – ከሚዛን ጣቢያችን

More Stories
የኮንታ ዞን ም/ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ ሥራ ዘመን 26ኛው መደበኛ ጉባኤው ተጠናቀቀ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
አጫጭር የሙያ ክህሎት ስልጠና ማግኛታቸው በሚሰማሩበት የውጭ ሀገራት ሁሉ ተግባራቸውን እንዲወጡ እንደሚያስችላቸው በሆሳዕና ከተማ የሚገኙ ሰልጣኞች ተናገሩ