የአርሶአደሩን የማምረት አቅም በማጎልበት የመስኖ አውታር ውጤታማነትን ለማጉላት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን በዳውሮ ዞን የኢሠራ ወረዳ ግብርና ህብረት ሥራ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት አስታወቀ
በበጋው ወቅት የማምረት ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ስለመምጣቱም አርሶአደሮች ተናግረዋል፡፡
በወረዳው የጋሹሜ አነስተኛ መስኖን በመጠቀም የበጋ መስኖ ስንዴ በማምረት ተጠቃሚ መሆናቸውን አርሶአደር ወርቁ ገበየሁ እና አርሶአደር ማሞ አበራ ተናግረዋል።
አሁን ላይ የመስኖ ተግባራት በመጀመራቸው ያለውን አማራጭ በመጠቀም ምርታማ እየሆኑ ስለመሆናቸው የገለጹ ሲሆን ይኸውም በአመት ሁለት ጊዜ እንዲያመርቱ እድል የፈጠረ ነዉም ብለዋል።
ምርታማነታቸውን ይበልጥ ለማሳደግ ሙያዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው ስለመሆኑ አንስተዉ ማሳቸዉን ከበሽታ ለመጠበቅ እንዲቻል የጸረ-አረምና የዋግ ርጭት በወቅቱ እንዲቀርብላቸውም ጠይቀዋል።
የአሩስ አንገላ ቀበሌ የግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ዴባንቾ በቀቤለዉ ያለዉን የመስኖ አውታርን በመጠቀም የአርሶ አደሩን የማምረት አቅም እና ፍላጐትን ከመመለስ አኳያ ተግባራት ተጠናክሮ ስለመቀጠላቸው ገልጸዋል።
ይህው የነበረውን የአመራረት ዘይቤ ከመቀየር ባሻገር አርሶ አደሩ ዘንድ አሁን ላይ መነሳሳት የፈጠረ በመሆኑ በቀበሌዉ በዘንድሮ ዓመት 270 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እስካሁን ባለዉ አፈጻጸም 212.5 ሄክታር መሬትን በዘር ለመሸፈን ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በዳውሮ ዞን የኢሠራ ወረዳ ግብርና ህብረት ሥራ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በቀለ በጋጆ፤ አሁን ላይ በወረዳው አርሶ አደሮች ዘንድ ለመስኖ ልማት ተግባራት ያለውን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ በተሠራው ሥራ ለውጥ ማምጣት ስለመቻሉ ተናግረዋል።
በዘንድሮ የበጋ መስኖ ስንዴ በወረዳዉ ከ1200 ሄክታር በላይ ማሳ በበጋ መስኖ ስንዴ ለመሸፈን እቅድ ተይዞ አሁን ላይ 875.5 ሄክታር በዘር መሸፈ መቻሉን ተናግረዉ ቀሪዉን ተግባራት ከግብርና ባለሙያዎችና ከአርሶአደሩ ጋር በጋራ በመሆን እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል፡፡
ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር በደረሰዉ ሰብል ላይ ጉዳት እንዳያጋልጥ የጸረ ተባይና ጸረ አረም አቅርቦትን ለአርሶሰደሩ ለማቅረብ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በጋራ በመሆን እየተሰራ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡ አዲስዓለም ታዬ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
ምርታማነትን የሚያሳድጉ የግብርና ቴክኖሎጂዎች በወቅቱ እንዲቀርቡ ተጠየቀ
በክልሉ ከበዓል ጋር ተያይዞ ሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖርና ጤናማ የግብይት ስርዓትን ለመፍጠር እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ
ከ800 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ማሰራጨቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ