ዘመናዊ የመሬት ሕግ ሥርዓት መዘርጋትና ተቋማዊ አቅምን መገንባት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 06/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ዘመናዊ የመሬት ሕግ ሥርዓት መዘርጋትና ተቋማዊ አቅምን መገንባት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሬት አስተዳደር ቢሮ ከግብርና ሚኒስቴር እና ከጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሕግ ማዕቀፍ ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል።
በግብርና ሚኒስቴር የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ትዕግስቱ ገብረመስቀል፥ የመሬት አስተዳደር ጉዳይ ልዩ ትኩረትና ድጋፍ የሚሻ የልማት ዘርፍ መሆኑን ገልጸዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሬት አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ዮሴፍ ማሩ በበኩላቸው፥ የመሬትን ፋይዳ ያገናዘበ የሕግ ማዕቀፍና አደረጃጀት ማስፈለጉን ተናግረዋል።
በGIZ ኢትዮጵያ የመሬት አስተዳደር ፕሮጀክት የፖሊሲና የሕግ አማካሪ ዶ/ር ዳንኤል በኃይሉ በበኩላቸው፤ ግልጽ ሕግ እንዲሁም የማስፈፀም አቅም ያለው አደረጃጀትና የሰው ኃይል መኖሩ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚስተዋሉ በርካታ ችግሮችን እንደሚፈታ ገልጸዋል።
የሕግ ማዕቀፍ ሰነዱን ካቀረቡት ባለሙያዎች መካከል በክልሉ የመሬት አስተዳደር ይዞታ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ጳውሎስ ባርጉዴ እንደገለጹት፥ የክልሉ መሬት አስተዳደር ቢሮ እንደ አዲስ መዋቀሩን ተከትሎ አዲስ የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትም የሚወጡ ሕጎችን ከሌሎች ነባር ሕጎች ጋር እንዲናበቡ መደረግ እንዳለበት ጠቁመው፥ መካተት በሚገባቸው ነጥቦች ላይ አስተያየቶች ተሰጥቷል።
ዘጋቢ: አማሮ አርሳባ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ