በክልሉ ከበዓል ጋር ተያይዞ ሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖርና ጤናማ የግብይት ስርዓትን ለመፍጠር እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ ከበዓል ጋር ተያይዞ ሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖርና ጤናማ የግብይት ስርዓትን ለመፍጠር እየተሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ።
በዓልን ምክንያት በማደረግ ከባዕድ ነገሮች ጋር ተቀላቅሎ የሚቀርቡ ምርቶችና አላስፈላጊ ጭማሪ ሊኖር ስለሚችል ሸማቾች ለሚመለከተው አካላት በማሳወቅ የድርሻቸውን እንዲወጡም ተጠይቋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትልና የንግድ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አምዴ ፋሪስ እንደገለፁት፥ በክልሉ ከበዓል ጋር ተያይዞ ሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖርና ጤናማ የግብይት ስርዓትን ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል።
በበዓል ወቅት በእንስሳት፣ በሰብል፣ በአትክልትና በፍራፍሬ ዘርፎች የምርት እጥረት እንዳይኖር በአቅርቦት መሻሻል ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል።
በክልሉ ባሉት አከባቢዎች ከበዓል ጋር ተያይዞ በምርቶች ላይ የሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ በሚታይበት ጊዜ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎችን የመውሰዱ ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ አምዴ አብራርተዋል።
በበዓል ግብይት ወቅት በቅቤ፣ በርበሬና በማር ምርቶች ላይ ባዕድ ነገሮችን የመቀላቀል ሂደት በሚፈጠርበት ጊዜ ህብረተሰቡ ለሚመለከተው የህግ አካላት ጥቆማ በመስጠት ከንግድ ተቋማት ጋር በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ኃላፊው ተናገረዋል።
በተለይም በቁም እንስሳት ግብይት ማዕከላት ህገ ወጥ ደላሎች ተጨማሪ እሴት የማይጨመሩ በመሆናቸው እንዲህ ዓይነት ተግባራት ሲኖር በጋራ መከላከል እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ አምዴ፥ ለመላው የክልሉ ህብረተሰብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
ግብር ለከተማው ብሎም ለሀገር ልማት ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት ለደንበኞቻቸው ደረሰኝ በመስጠት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እየተወጡ መሆናቸውን በንግድ ሥራ ላይ የተሠማሩ ግብር ከፋዮች ተናገሩ
ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ ገለፀ
ገቢ ከራስ ለራስ የሚዉል በመሆኑ በቴክኖሎጂ በተደገፈ የአከፋፈል ስርዓት በአጭር ቀናት ከታቀደው በላይ ግብር መሰብሰብ እንደሚገባ ተገለጸ