50ኛው የኢትዮጵያ ሴቶች ቀን (ማርች 8) በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ እየተከበረ ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን “የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በመከበር ላይ ነው።
በመርሀ ግብሩ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ ፣ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ዶክተር ዳዊት ሀዬሶ ፣ የክልሉ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ ታድመዋል።
ከዚህ ባሻገር ከፌደራል ከክልል፣ ከዞን የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሴት አደረጃጀት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመርሃ ግብሩ ላይ እየተሳተፉ ናቸው።
በፓናል ውይይት የሚከበረው ይህ የሴቶች ቀን በዓል በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሴቶችን ጀግንነትና አይበገሬነት የሚያወሱ ሙዚቃዎች ፣እንስቶች በሀገር ግንባታ ላይ ያሳረፉትን አሻራ የሚያስታውሱ ስነ-ግጥሞችና በብሄር ብሔረሰቦች የባህል ዜማዎችና መሠል ደማቅ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።
ዘጋቢ :- አብደላ በድሩ

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ