በ75 ሄክታር መሬት ላይ እየለማ ያለ የስንዴ ምርጥ ዘር ብዜት ቴክኖሎጂ ማስተዋወቅና የተግባር መስክ ምልከታ ተካሔደ
ሀዋሳ፡ ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአሪ ዞን ሰሜን አሪ ወረዳ በ75 ሄክታር መሬት ላይ እየለማ ያለ የስንዴ ምርጥ ዘር ብዜት ቴክኖሎጂ ለማስተዋወቅና የተግባር መስክ ምልከታ መካሔዱ ተገለጸ፡፡
የጅንካ ግብርና ምርምር ማዕከልና የሰብል ዝርያ ማሻሻያ ከፍተኛ ተመራማርና የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶ/ር ተክሌ ዮሰፋ እንደገለፁት፥ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ 14 ዓይነት የስንዴ ዘር ሙከራ በማድረግ ከአከባቢው ጋር ተስማሚ የሆነውን የ‘ኦኮልቾ’ ስንዴ ዝርያ በማባዛት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በወረዳው ሻንጋማ ፃክ እና ማጣ ዛብር ቀበሌ እየለማ የሚገኘው 75 ሔክታር የስንዴ ምርጥ ዘር ብዜት፥ 164 አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን ጠቁመው፥ ከአንድ ጥማድ ማሳ ከአራት ኩንታል በላይ እንደሚያገኙ የቀበሌው ሊቀመንበር ዮናስ እሸቱ እና አርሶ አደር ዳንኤል ሀይሌ ተናግረዋል።
የሰሜን አሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታፈሰ ተስፋዬ እንደገለጹት በምርምር የተገኙት የልማት ቱርፋቶች አበረታች በመሆኑ ለአርሶ አደሮች የግንዛቤ ስራ ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።
የታየዉ የምርጥ ዘር ብዜት ለሁሉም ማህበረሰብ ሊዳረስ የሚገባና የታየው ውጤትም አበረታች መሆኑን የአሪ ዞን ዋና የመንግስት ተጠርና የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጉራልቅ ይዥማልቅ ገልፀዋል።
የኑሮ ውድነትንና የገበያ መረጋጋት ስራ ላይ የሃገራችን ጀርባ አጥንት የሆነዉን የግብርና ስራ በቴክኖሎጂ በማስደገፍ መስራት እንደሚጠበቅ የታየው ምርት አበረታች መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ተመስገን ንፍርቄ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በክልሉ ከበዓል ጋር ተያይዞ ሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖርና ጤናማ የግብይት ስርዓትን ለመፍጠር እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ
ከ800 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ማሰራጨቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ
ከወልቂጤ – ጉብሬ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ህጉን ተከትለው የሚሰሩና የህብረተሰቡን ችግር የሚቀርፉ መሆናቸው ተጠቆመ