ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ በተጋጣሚዎቻቸው ተሸነፉ

ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ በተጋጣሚዎቻቸው ተሸነፉ

በ19ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ መርሐግብር ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ በተጋጣሚዎቻቸው ተሸንፈዋል።

በሜዳው ኒውካስልን ያስተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ 2ለ0 በሆነ ውጤት ተረቷል።

ለኒውካስል የማሸነፊያ ግቦችን አሌክሳንደር ኢሳቅ እና ጆይሊንተን ከመረብ አሳርፈዋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ45 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪሚዬርሊጉ በሜዳው በ3 ተከታታይ ጨዋታዎች ተሸንፏል።

ከሜዳው ውጪ ኢፕሲች ታውንን የገጠመው ቼልሲም በተመሳሳይ 2ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ለኢፕሲች ታውን የማሸነፊያ ግቦችን ሊያም ዴላፕ እና ሆቺንሰን አስቆጥ።

አዲስ አዳጊው ክለብ በውድድር ዓመቱ በሜዳው የመጀመሪያ ድሉን ነው ማሳካት የቻለው።

በሌላ ጨዋታ አስቶንቪላ ከብራይተን ያከናወኑት ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

በሙሉቀን ባሳ