በክልሉ የተጀመረውን የልማት እና መልካም አስተዳደር ሥራዎችን በማጠናከር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከግጭት የጸዳ አካባቢ ለመፍጠር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላም እና ፀጥታ ቢሮ አሳሰበ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሠላም እና ፀጥታ ቢሮ ለዞኖች እና ሪጂዮ ፖሊ ከተማ አስተዳደሮች የሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊዎች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች በግጭት መከላከል እና አፈታት ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላም እና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አቤንኤዘር ተረፈ፤ የሠላምና ፀጥታ ጉዳይ ለአንድ ወገን የሚተው አለመሆኑንና የበቃ አመራር እና ባለሙያዎች ግጭቶችን አስቀድመው እንዲከላከሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ያግዛል ብለዋል።
የክልሉን ሠላም በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ያሳሰቡት የቢሮ ሀላፊው፤ ክልሉ የዳበረ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ያሉት በመሆኑ የተጀመረውን ልማትንና ሠላም ለማስቀጠል ከግጭት ነጻ የሆነ አካባቢን ለመፍጠር በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውንም ሀላፊው ገልጸዋል።
በስልጠና መድረኩ ላይ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች እና ሪጂዮ ፖሊ ከተሞች የተወከሉ አመራሮች እና ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
በዘመናዊ መንገድ ንብ የማነብ ስራ በመጀመር ውጤታማ መሆናቸውን በወላይታ ዞን የዳሞት ወይዴ ወረዳ ወጣቶች ተናገሩ
አሽራፍ ሀኪሚ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ሕዳር 08/2018 ዓ.ም