የብልፅግና ፖርቲ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞንና በዲላ ከተማ አስተዳደር የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክትና ማኒፌስቶውን የማስተዋወቂያ መርሀ ግብር በዲላ ከተማ አካሂዷል።
ፓርቲው “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፖርቲ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶ አስተዋውቋል።
በመርሀ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጌዴኦ ዞን የብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ኢንጂነር ተመስገን ጥላሁን፥ እንደ ሀገር ኢትዮጵያን ማሻገር የሚችሉ በርካታ ተግባራት መካከል ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ብሎም የኢኮኖሚ ሪፎርም ሥራን ውጤታማ በማድረግ ሂደት በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሀገረ መንግስት የማሰቀጠልና የተጀመሩ አዳጊ ሥራዎች ኢትዮጵያን ወደ ዕድገት ማማ የሚያሻግሩ መሆናቸውን አውቆ መሥራት ይጠይቃልም ተብሏል።
በሀገር ደረጃ ለዘመናት ጥያቄ ሆነው ለቆዩ ጉዳዮች ምላሽ የተሰጠበት፣ ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎች፣ ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምን በማፅናት የሽግግር ፍትህ የተረጋገጠበት መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪ ቃል የምግብ ሉዓላዊነትን ሊያረጋግጥ የሚችል የስንዴ ነዶ የምርጫ ምልክት መሆኑን ኢንጅነር ተመስገን አብስረዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዲላ ከተማ አስተዳዳሪ መስፍን ደምሴ(ዶ/ር) እንደ ሀገር በርካታ አሉታዊ ችግሮችን በመፍታት አሰባሳቢ ትርክትን በመገንባት እየሠራ የሚገኝና ህዝባችን በፍትሀዊነት የማደግና የመለወጥ ብሎም የመልማት ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት በርካታ የሪፎርም ሥራዎችና እኒሼቲቮች ተቀርፀው ወደ ተግባር በመግባት ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል።
አክለውም የኢትዮጵያን የጂኦ ፖለቲካ ቁመና ለማምጣትና ከተሞችን ለነዋሪ ምቹ ከማድረግ ረገድ ከተማና ገጠርን በማስተሳሰር ለአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት የሆነችባቸው ጊዜያት ነበሩ ሲሉ ዶክተር መስፍን አንስተዋል።
የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) የለውጡ መንግስት እንደሀገር የገጠመንን የፖለቲካ ስብራት በማከም በአካታችና አቃፊነት መርህ መሠረት በርካታ ተግባራት እንደተከናወኑ ጠቁመው በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚውና በፖለቲካው ዘርፎች እምርታ ለውጦች መመዝገባቸውንና የማህበረሰቡን የመልማት ጥያቄን የመመለስ ሥራዎች ተመዝግበዋል ብለዋል።
በሀገራችን የተረጋጋ ሠላም እንዲሰፍንና ሉዓላዊነታችንን በማረጋገጥ የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በመከላከል በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ መነሻ እራስን በመቻል፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ ምርትንና ምርታማነትን በማረጋገጥ በግብርናው ዘርፍ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታን ጨምሮ የውሃ ሀብታችንን በመጠቀም ለዓለም ተምሳሌትና የቱሪዝም መዳረሻ የሆንበት ነው ብለው ሀገራችን የብልፅግና ተምሳሌት የሆነችበትን የፖርቲው መወዳደሪያ ማኒፌስቶ የምርጫ ምልክት የስንዴ ነዶ መሆኑን አስረድተዋል።
አንደሀገር የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት በርካታ ለውጦች የተመዘገቡበት መሆኑን አስታውሰው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ ሠላማዊና ፍትሀዊ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ የመርሀ-ግብሩ ተሳታፊዎች አንስተዋል።
ዘጋቢ: ፅጌ ደምሴ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የጎፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል
በበጋ መስኖ የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችን እና ፍራፍሬዎችን በማልማት ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውን በዳውሮ ዞን ከጪ ወረዳ የከጪ ቱታ ቀበሌ አርሶ አደሮች ገለጹ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አከራካሪ የሆኑ ምርጫ ክልሎችን በተመለከተ ውሣኔ አስተላለፈ