“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ የምርጫ ምልክት “የስንዴ ነዶ” ሲሆን ምልክቱ የመደመር፣ አንድነት እና ትብብር መገለጫዎችን የያዘ መሆኑን ተገልጿል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ግዛው እንደገለጹት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፓርቲው አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች የሚጠበቅባቸውን ሚና በተገቢው መወጣት ይገባቸዋል።
ፓርቲው እንደ አንድ ፓርቲ በምርጫው ከመወዳዳር ባለፈ ምርጫው ነፃ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግስታዊ የሆነ ድርብ ኃላፊነት ያለው መሆኑንም አቶ ታምራት አንስተዋል።
ለምርጫው ስኬታማነት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ የመስራት ኃላፊነቱን ፓርቲው በትኩረት እንደሚወጣ በአጽንኦት ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮን ጨምሮ የዞን፣የወረዳና የከተማ ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች፣አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ: ኤርጡሜ ዳንኤል – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው