ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የእግርኳስ ክለብ ድርሻ ባለቤት መሆኑን አሳውቋል።
የአምስት ጊዜ የባሎንዲኦር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ የስፔኑ ክለብ አልሜሪያ 25 በመቶ ድርሻ መግዛቱ ይፋ ሆኗል።
ክለቡ አሁን ላይ በሳውዲ አረቢያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትነት ተይዞ በመተዳደር ላይ ይገኛል።
በፈረንጆቹ 1989 የተመሰረተው አልሜሪያ በስፔን ሁለተኛ የሊግ ዕርከን እየተወዳደረ የሚገኝ ሲሆን ከመሪው ሪያል ሬሲንግ በሁለት ነጥቦች አንሶ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ከላሊጋው ወደ ሴጉንዳ ዲቪዚዮኑ የወረደው።
የ41 ዓመቱ ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በስፔን በስኬት ታጅቦ ስኬታማ ዘጠኝ ዓመታትን ማሳለፉ ይታወሳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።