የዋካ ከተማ አስተዳደር የባለ አደራ ምክር ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ለመጪው ገና በዓል ለእርድ የሚሆን የቁም ከብት በብዛት ለማቅረብ መዘጋጀቱን አስታወቀ
ሦስተኛ ሣምንቱን በያዘው የዋካ ቅዳሜ የቁም ከብት ገበያ ግብይቱ እንደበፊቶቹ ሣምንታት ሁሉ በደራ ሁኔታ ቀጥሏል።
በገበያው ሰንጋ በሬዎች ከሰላሳ እስከ ሃምሳ ሺህ ብር እየተሸጡ ያለ ሲሆን ሙክት በግና ፍየሎች ደግሞ ከአስራ አምስት እስከ ሃያ አምስት ሺህ በመገበያየት ላይ ነው የሚገኙት።
ከዚሁ ጎን ለጎን በገበያው ለመጪው ገና በዓል የሚሆኑ ሰንጋ በሬዎች እና ሙክት በግና ፍየሎችን ለሸማቾች በብዛት ለማቅረብ ከአቅራቢ ባለድርሻዎች ጋር በመሆን እየሰራን ነው ሲሉም የከተማዋ አስተዳደር ባለ አደራ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት አቶ እስክንድር ተፈራ ተናግረዋል።
በገበያው አግኝተን ያነጋገርናቸው በርካታ ሻጭና ገዢዎች በሰጡት አስተያየት፣ ቅዳሜ ዕለት የሚቆመው ይኸው የዋካ ገበያ ከሣምንት ወደ ሣምንት እየደራ መሆኑን ገልጸው፣ ገበያው ገና ጅምር ላይ እንደመሆኑ በሁለት እግሩ እስኪቆም ድረስ ትርፍን መሠረት አድርገን ሳይሆን ለከተማዋ መልማት አጋዥ አንዲሆን ስንል በተለይ ገበያውን ለማጠናከር እንሰራለን ብለዋል።
ያነጋገርናቸው ሰንጋና ሙክት አቅራቢዎችም በቂ አቅርቦት ያለ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ከተማዋን የበለጠ ለማልማት በቀጣይ ባዛር ለማዘጋጀት የባለ አደራ ምክር ቤቱ እቅድ መያዙንም አስታውቋል።
በእቅዱ መሠረት ባዛሩ ከጥር 3 እስከ 6/2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ በዋካ ከተማ የሚደረግ ሲሆን በወቅቱ የልማት አጋሮች የሆኑት ሁሉ በመገኘት አጋርነታቸውን እንዲገልፁም የባለ አደራ ምክር ቤቱ ጥሪ አስተላልፏል።
ዘጋቢ፡ አሸናፊ ግዛው – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
የሀለባ ዞን ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ቢልዮን 293 ሚልዮን ብር ባለይ በጀት አጸደቀ
መስራት እየቻሉ የገንዘብ እጥረት የገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግሮች ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ቀላል አለመሆኑ ተገለጸ
በስልጤ ልማት ማህበር ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር የተሰበሰቡ የአካባቢው ተወላጆች በዞኑ በሚገኙ የላንፉሮ ወረዳና ጦራ ከተማ አስተዳደር ችግኞችን ተክለዋል ።