ከ346 ሺህ ኩንታል በላይ ቡናን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅርብ እየተሰራ እንደሚገኝ የቤንች ሸኮ ዞን ግብርናና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ሥራ መምሪያ አስታወቀ
በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ ከ35 ሺህ ሄክታር በላይ የቡና ማሳ ያለ ሲሆን ከ25ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ ምርት የሚሰጥ መሆኑን የወረዳው ምክትል አስተዳደሪና የግብርናና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ሥራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኪዳነ ሽቅ ተናገረዋል።
ወደ ማዕከላዊ ገበያ የሚላከውን የቡና ምርትን ከማሳደግ አኳያ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ በሄክታር
ከ7 እስከ 9 ኩንታል ምርት እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ኪዳኔ በጀንፈል ሲሆን በሄክታር ከ25 እስከ 30 ኩንታል ይገኛል ብለዋል።
በወረዳው በስፋት ከሚመረተው ከቡና ምርት ጎን ለጎን ቅመማ ቅመም ትኩረት ተሰጥተው የሚሰራ ሲሆን ኮረሪማ፣ ቁንዶ በረበሬ፣ ዕረድ እና ዝንጅብል ተጠቃሾች መሆናቸውን ኃላፊው አብራርተዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡናን በብዛትና በጥራት ከሚያመረቱ ዞኖች መካከል የቤንች ሸኮ ዞን አንዷ መሆኗም ተገልጿል።
በበጀት ዓመቱ ከ346 ሺህ ኩንታል በላይ ቡናን ለአለም ገቢያ ለማቅርብ እየተሰራ እንደሚገኝ የዞኑ ግብርናና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ ተናገረዋል።
ዘጋቢ፦ አብዲሳ ዮናስ ከሚዛን ጣቢያችን።

More Stories
የሀለባ ዞን ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ቢልዮን 293 ሚልዮን ብር ባለይ በጀት አጸደቀ
መስራት እየቻሉ የገንዘብ እጥረት የገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግሮች ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ቀላል አለመሆኑ ተገለጸ
በስልጤ ልማት ማህበር ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር የተሰበሰቡ የአካባቢው ተወላጆች በዞኑ በሚገኙ የላንፉሮ ወረዳና ጦራ ከተማ አስተዳደር ችግኞችን ተክለዋል ።