አርብቶ አደሩ በማህበርሰብ አቀፍ የጤና መድህን አግልገሎት ይበልጥ ተጠቃሚ በማደረግ ከድንገተኛ የህክምና ወጪ ለመታደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
ሀዋሳ፡ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምርያ የ2017 በጀት አመት የማህበርሰብ አቀፍ የጤና መድህን ንቅናቄ እንዲሁም የመከፈል አቅምን መሰረት ያደረገ መዋጮና የዞን የጋራ ቋት አመሰራረት ዙርያ ላይ የግንዛቤ ማሰጨበጫ መድረክ በድመካ ከተማ ተካሂዷል።
በንቅናቄ መደረኩ ላይ ተገኘተዉ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማልኮ እንደገለፁት እንደ ዞን በጤናዉ ዘርፍ ያሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ እንደ ዞን ፍታዊ የሆነ የጤና መድን አግልገሎትን ለማህበርሰቡ ተደራሸ በማደረግ ማህበርሰብ አቀፍ ጤና መድህን አግልገሎት ለሁሉም ተደራሸ እንድሆን በቀጣይ አሰፈላግዉን ድጋፈ በማደረግ አግልገሎት አሰጣጡ ዉጤታማ እንድሆን በትኩረት እንደሚሰራ ግልፀዋል።
እንደ አርብቶ አደር አከባቢ ማህበርሰብ አቀፍ የጤና መድህን አግልገሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ መሆኑና የጤና መድህን ሥራን በባለቤትነት ተግባሩን እየመሩ ያሉ መዋቅሮች በመፈጠራቸዉ አኳያ ዞኑ ተሸላም መሆን መቻሉን የገለፁት ዋና አሰተዳዳሪዉ በተገኘው የተሻለ አፈፃፀም ትልቅ ደሰታና ስኬት የታየበት አመት እንደመሆኑ መጠን በቀጣይም ይህን አጠናክረዉ በማሰቀጠል በተዋረድ ሁሉም መዋቅሮች ማህበርሰብ አቀፍ የጤና መድህን ሥራዉን ማሰተባበረና ማሳካት እንደሚገባ ገልፀዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምርያ ኃላፊ አቶ ታምራት አሰፋ እንደገለፁት በ2010ዓ.ም ጀምሮ በጤና መድህን አገልገሎት በማህበረስቡ ዘንድ በይፋዊ መልኩ በማሰጀመረ በአርብቶ አደሩ አከባቢ የማይቻል የሚመሰለዉን የጤና መድህን አግልገሎት ማሳካት እንድቻል ከፍተኛ ርብረብ በማደረግ ዉጤታማ መሆን መቻላቸዉንና በ2016ዓ.ም በልዩ ሁነታ በጤና መዋቅር ባለሙያዎች አመራሮች ከዚያም ባሻገር ከዞንና ከክልል ልዩ ድጋፈና ክትትል በመደረጉ ዉጤታማ መሆን መቻላቸዉን ተናግረዋል።
ኃላፊው አክለውም በአጠቃላይ ምጣኔ 64 ከመቶ እድሳትና አድሰ አባል የማፈራት ጉዳይ እንድሁም መክፈል የማይችሉ አካላት የተናጥል ድጎማ በማደረግ 2015ላይ 64ከመቶ ከነበረበት በ2016 ዓ.ም 81ከመቶ ማሳካት መቻላቸዉንና የእድሳት ምጣኔዉም 92ከመቶ ማደረሰ የተቻለበትና ዉጤታማ የሆነ የማህበርሰብ አቀፍ ጤና መድን ፕሮገራም መደረጉን ግልጿል።
በንቅናቄ መደረኩ ላይ የተገኙት አሰተያየት ሰጭዎች እንደገለፁት ማህበርሰቡ የማህበርሰብ አቀፍ ጤና መድህንን በበጎ መልኩ ተቀበለዉ የአገልገሎቱ ተጠቃም ቢሆኑም በማህበርሰብ አቀፍ ጤና መድህን አግልገሎት አሰጣጥ ዙሪያ አግልገሎት አሰጣጡን የተሳካ ለማደረግ የሰዉ ሀይል እና የመደኃንት እጥረት እንቅፋት እንደሆነባቸዉ ገልፀዉ በቀጣይ ይህ ችግር ልፈታ ይገባልም ብለዋል።
ከተሳታፊዎች በተነሱ ጉዳዮች ዙርያ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማልዕኮና የዞኑ ጤና መምርያ ኃላፊ አቶ ታምራት አሰፋ በምላሻቸዉ ከጤና መድህን አገልገሎት አሰጣጥ ዋነኛ ችግሮች የግብዓት አቅርቦት እና የሰዉ ኃይል አለመሟላት ችግር ለመፍታት በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ይሆናሉ ብለዋል።
በመደረኩ በማህበርሰብ አቀፍ ጤና መድህን የተሻለ አፈፃፀም ላደረጉ ወረዳዎችና አካላት የዋንጫና የእዉቅና ምሰክር ወርቀት ተበረክቶላቸዋል
ዘጋቢ ፡ ግዳጁ ጎሮጊ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመከላከልና የተጣሉ ግቦችን ለማሳካት ትኩረት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአገርቷ ለሚካሄደው የሰላምና የልማት ተግባራት ላይ አባላቱ የድርሻቸውን እንዲወጡ ተገቢውን የማስተባበርና የማቀናጀት ሥራ እያከናወነ መሆኑን ተገለጸ
የአንጀት ጥገኛ ትላትል በሽታ የህብረተሰብ ስጋት በማይሆንበት ደረጃ መቆጣጠር መቻሉ ተጠቆመ