የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአገርቷ ለሚካሄደው የሰላምና የልማት ተግባራት ላይ አባላቱ የድርሻቸውን እንዲወጡ ተገቢውን የማስተባበርና የማቀናጀት ሥራ እያከናወነ መሆኑን ተገለጸ
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ” መመርመር ራስን ለማወቅ፣ ቅዱሳት መጽሐፍት የፀረ-ኤችአይቪ መውሰድን ይፈቅዳሉ ” በሚል መርህ ሀሳብ ማህበረሰቡ በጸረ ኤች-አይቪ ኤድስ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳትፎውን እያጎለበተ እንዲሄድ የሚያስችል የምክክር መድረክ አካሂዷል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሰባት የሃይማኖት ተቋማት የተቋቋመ ነው።
በአገርቱ ለሚካሄደው የሰላምና የልማት ተግባራት ላይ አባላቱ የድርሻቸውን እንዲወጡ ተገቢውን የማስተባበርና የማቀናጀት ሥራ ዓላማ አድርጎ እያከናወነ መሆኑን በኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የባህርይ ለውጥና ተግባቦት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ በድር አደም ገልጸዋል።
ተቋሙ ከአሜሪካ መንግስት ተራድኦ ድርጅት (USAID) ” Faith based retention and adherence Intervention” የሚባል ፕሮጀክት በናሽናል አሶስዬሺን በኩል ግንኙነት በማድረግ ወደ ሥራ መግባቱን አቶ በድር ጠቁመዋል ።
ከዚህ ጋር አያይዘው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የአድቮከስ ፣የተግባቦትና የማህበረሰብ ንቅናቄ ዘዴዎችን በማጠናከር ማህበረሰቡ በጸረ-ኤች አይቪ ኤድስ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚያደርገውን ተሳትፎ ማጠናከር እንዲችል የምክክር መድረክ መካሄዱን አቶ በድር ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ ከሃይማኖት አባቶች ከከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች እና ኤች-አይቪ በደማቸው የሚገኝባቸው ወገኖች ማህበራት አስተባባሪዎች ክልላዊ የአድቮከሲ ምክክር መድረክ ላይ በመሣተፍ ዓላማው ስኬታማ እንዲሆን የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል እንደሆነ አስረድተዋል ።
የመድረኩ መርህ ሀሳብ ” መመርመር ራስን ለማወቅ፣ ቅዱሳት መጽሐፍት የፀረ-ኤችአይቪ መውሰድን ይፈቅዳሉ ” በሚሉት ላይ ያተኮረ ነው።
በመድረኩ ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃም ሆነ አንደክልል የኤችአይቪ ኤድስ ሥርጭት መጠን ያለበትን ሁኔታ የሚዳስስ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
በዚህ መሠረት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከ14ሺ በላይ የሚሆኑ ወገኖች ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ የተገለጸ ሲሆን በክልሉ ከሚኖረው ማህበረሰብ 95 በመቶ የሚሆነው ተመርምረው ራሳቸውን እንዲያውቁ ከማድረግ አኳያ በትጋት መሠራት እንዳለበት ተመክሯል።
ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ወገኖች የጸረ-ኤች አይቪ መድኃኒትን በሐኪም ትዕዛዝ ብቻ በቋሚነት መውሰድ እንዳይችሉ እንቅፋት የሚሆኑባቸውን ጉዳዮችና መፍትሄዎቻቸውን ከሃይማኖት አስተምሮ አንጻር በመዳሰስ በቀጣይ የተሻለ ሥራ ለማከናወን የሃይማኖት ተወካዮች ቃል በመግባት ለትግበራ ምዕራፍ አቅጣጫ አመላክቷል።
አዘጋጅ ፡ መለሰ ገብሬ-ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
የአንጀት ጥገኛ ትላትል በሽታ የህብረተሰብ ስጋት በማይሆንበት ደረጃ መቆጣጠር መቻሉ ተጠቆመ
ከማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የወጣውን ገቢ መሰረት ያደረገ የስላይዲንግ ስኬል ለመተግበር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ
የወባ በሽታ ስርጭት ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሚገኙ ተጠቆመ