መጪው ጠቅላላ ምርጫ ተአማኒና በህዝቡ ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆን በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ደሣለኝ ገለፁ
የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ ማኒፌስቶ የክልልና የዞን አመራሮች፣ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለምብርሃን ካሳሁን፥ ኢትዮጵያ ለዘመናት የገጠሟትን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ስብራቶች በሪፎርም በማከም ጠንካራ ፓርቲና መንግሥት የመገንባት ተልዕኮዋን በብቃት እየተወጣች ትገኛለች ብለዋል።
በኢኮኖሚው ዘርፍ ሀገር በቀል ሪፎርሞችን ተግባራዊ በማድረግ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ከመፍጠር ባለፈ፥ የገበያ ሥርዓቱን ፍትሐዊና ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ስልታዊ እርምጃዎች እንደተወሰዱ ገልጸዋል።
ከዲፕሎማሲው ረገድም ከነበረብን ተከልካይ አካሄድ ወጥተን የሀገራችንን ሉዓላዊ ጥቅም የሚያስከብር የጋራ ተጠቃሚነት መርሆን በመከተል ታላላቅ ድሎች መመዝገባቸውን አቶ አለምብርሃን አንስተዋል።
በተለይም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ኢትዮጵያውያን በአፍሪካ ቀንድ አዲስ ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ትርክትና ዳግማዊ የዓድዋ ድል የማስመዝገብ አቅም እንዳለን ለዓለም ያሳየንበት የታሪካችን ወርቃማ ምዕራፍ ሆኗል ብለዋል።
የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ በማዳመጥ በመልማት አማራጮች ላይ ጊዜ ወስዶ በማሰብና በመለየት የአጭር፣ የመካከለኛ እና ረጅም ጊዜ ዕቅድ በማዘጋጀት ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ አመላክተዋል።
ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠልና ለ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት፣ እንደ ብልፅግና ፓርቲና መንግሥት አስቻይ ሁኔታ የመፍጠርና እንደ ተወዳዳሪ ፓርቲ ደግሞ በአሽናፊነት የመውጣት ድርብ ኃላፊነት ይጠብቅብናል ብለዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ደሳለኝ በበኩላቸው ባለፉት ጊዚያት እንደሐገር የማይደፈሩ የሚመሥሉ ልማታዊ አጀንዳዎችን ፓርቲው ደፍሮ መፈጸም መቻሉንና በቀጣይም እንደሚፈጽም ተናግረዋል።
የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ሰፋፊ የኢኮኖሚ ሪፎርሞች መደረጋቸውን ያነሱት አስተዳዳሪው በገጠርና በከተማ የተያዙ ልማታዊ ኢኒሼቲቭ አጀንዳዎችን አመርቂ ውጤት አስመዝግቧዋል ብለዋል።
ፓርቲው የሚከተለው አካታች የዲሞክራሲ እይታ በአዲስ መልክ በተደራጀው ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባስኬቶ ዞን የፓለቲካዊ ተሳትፎና የልማት ተጠቃሚነት እንየዲጨምር ማስቻሉን ጠቅሰዋል።
የብልፀግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት የአብሮነት ተምሳሌት መሆኑን ያብራሩት አስተዳዳሪው ምርጫው በሠላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ጥረት ይደረጋል ብለዋል።
ዘጋቢ፡ አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ