የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 28ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል
በጉባኤው የግብርና ሥራ በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ከማረጋገጥ ረገድ የተሻለ ውጤት መመዝገቡ ተመላክቷል።
በመርሀ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ፀጋዬ ታደሰ እንደገለፁት እንደዞን ማህበረሰባችንን በልማት ሁሉ አቀፍ ተሳታፊና ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ ለውጦች መታየታቸውን አንስተው በቀጣይም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
አክለውም አፈጉባኤው 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ሠላማዊና፣ ፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የምክርቤቱ አባላት የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዶ/ር ዝናቡ ወልዴ በበጀት ዓመቱ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አኳያ ምርትና ምርታምነት የተሻለ ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል።
በዞኑ ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በቡና የተሸፈነ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ዝናቡ፥ ልማቱን ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰራ ሥራ የተሻለ ውጤትና ዕድገት መመዘገቡን አስረድተዋል።
የምግብ ዋስትናን ከማረጋጥ አንፃር ከ62 ሚሊዮን በላይ የእንሰት ችግኝ በማዘጋጀት ሌሎችም የተቀናጀ ግብርና ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አስተዳዳሪው አንስተዋል።
በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በጤና እና በትምህርት የተጀመሩ ለውጦችን ትኩረት በመስጠት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፥ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን በቀጣይ በትኩረት የሚሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በጉባኤው የተሳተፉ አካላት የግብርና ሥራዎችን ከማሻሻል፣ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግና የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ረገድ የተሻሉ ለውጦች መታየታቸውን አንስተው በትምህርት፣ በጤና፣ እንዲሁም የገቢ አቅምን አሟጦ ከመጠቀም አኳያ ያሉ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል።
በጉባኤው የክልል ከፍተኛ አመራር፣ የዞን አስተባባሪና አመራር አካላት፣ የባህል ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባትቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶቾ የታደሙ ሲሆን፥ የተለያዩ ሹመቶች በምክርቤቱ ፀድቀው ጉባኤው ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ ፅጌ ደምሴ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 28ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል

More Stories
በዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ዘርፍ በመሰማራታቸው የቤት ፍጆታን ከማሟላት ባሻገር በኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን በጋሞ ዞን ገረሴ ከተማ በዘርፉ የተሰማሩ አንዳንድ አካላት አረጋገጡ
ክቡር የሆነውን የሰውን ሕይወት ለመታደግ ደም በመለገስ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ የይርጋጨፌ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት አሳሰበ
ለሴቶች ሞት ምክንያት የሆነውን የማህፀን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራ በማድረግ መከላከል እንደሚገባ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የማህፀንና ፅንስ ሐኪም ዶ/ር አረጋኸኝ ሙሉጌታ አሳሰቡ