8 ወራትን ብቻ በሰሜን ለንደን የቆየው አሰልጣኝ
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶትንሃም ዋና አሰልጣኙን ቶማስ ፍራንክን ከሀላፊነት አሰናብቷል።
በውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኘው ቶትንሃም ትናንት ምሽት በሜዳው በኒውካስል 2ለ1 ከተሸነፈ በኋላ በማግስቱ ዴንማርካዊውን አሰልጣኝ ማሰናበቱን አሳውቋል።
ክለቡ በፕሪሚዬር ሊጉ ያለፉትን 8 ተከታታይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ አልቻለም።
በአሰልጣኙ መሪነት ከመጨረሻዎቹ 17 ሁለቱን ብቻ ያሸነፉት ስፐርሶች ከወራጅ ቀጠናው በአምስት ነጥብ ብቻ እርቀው በሊጉ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
የ52 ዓመቱ አሰልጣኝ ቶትንሃምን በሁሉም ውድድሮች በ38 ጨዋታዎች 13 ጨዋታዎችን ነው ማሸነፍ የቻሉት።
አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ከስምንት ወራት በፊት አሰልጣኝ አንጄ ፖስቴኮግሉን በመተካት ቶትንሃምን መረከባቸው ይታወሳል።
ቶትንሃም ተሰናባቹን አሰልጣኝ ለመተካት ስራዎችን መጀመሩ ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።