በ2016 ዓመተ ምህረት የምርት ዘመን የስንዴ ምርት በምን ያህል ከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ያውቁ ይሆን?
አነስተኛ ማሳ ተጠቃሚ ገበሬዎች 3.6 ሚሊዮን ሄክታር አርሰው 123 ሚሊዮን ኩንታል ሲያመርቱ በመስኖ ከታረሰው 2.9 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ደግሞ 107.7 ሚሊዮን ኩንታል ማምረት ተችሏል። የ2016 የኢትዮጵያ የስንዴ ምርት በድምሩ 230 ሚሊዮን ኩንታል ደርሷል።
ከ2012 የምርት ዘመን ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ማሳ ተጠቃሚ ገበሬዎቹ 54 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ብቻ ነበር ያመረቱት። ዛሬ ይህ ቁጥር ትርጉም ባለው መጠን ከፍ ብሏል። ይህ እመርታ በፅኑ አመራር፣ በአስቻይ ፖሊሲዎች ብሎም ምርትን ለማሳደግ በተተገበረ ያላሰለሰ ጥረት የተገኘ ነው። – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት
More Stories
የልማት ፍላጎት ማሟላት የሚቻለው በራስ አቅም ግብርን በአግባቡ መሰብሰብ ሲቻል እንደሆነ ተጠቆመ
በዓሉን ለማክበር የሚመጡ እንግዶች ደህንነታቸው ተጠብቆ በቆይታቸው ተደስተው እንዲመለሱ በትራንስፖርቱ ዘርፍ በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ
ከ148ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ እንደሚለማ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ