አርሰናል፣ባርሴሎና እና ባየርን ሙኒክ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ማንቸስተር ሲቲ ነጥብ ጥሏል
በአውሮፓ ሻምፒዮንስሊግ 5ኛ ዙር የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች አርሰናል ባርሴሎና እና ባየርን ሙኒክ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲረቱ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ነጥብ ጥሏል።
ከሜዳው ውጪ ስፖርቲንግ የገጠመው አርሰናል 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።
ለአርሰናል የማሸነፊያ ግቦችን ማርቲኔሊ፣ ሃቨርትዝ፣ማጋሌሽ፣ሳካ እና ትሮሳርድ ከመረብ አሳርፈዋል።
በአሊያንዝ አሬና ፒኤስጂን ያስተናገደው ባየርን ሙኒክ ኪም ምንጃኤ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ 1ለ0 ረቷል።
ባርሴሎናም በሜዳው የፈረንሳዩን ክለብ ብረስትን አስተናግዶ 3ለ0 አሸንፏል።
የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦችን ሮበርት ሊቫንዶውስኪ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቀሪዋን ግብ ዳኒ ኦልሞ ከመረብ አሳርፏል።
በኤቲሐድ ስታዲየም ማንቸስተር ሲቲ ከሆላንዱ ክለብ ፌዬኖርድ ጋር ባከናወነው ጨዋታ 3ለ0 ሲመራ ቆይታ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩበት ጎሎች አቻ ሆኖ ነጥብ ጥሏል።
በጨዋታው ለማንቸስተር ሲቲ ኤርሊንግ ሃላንድ ሁለት ጊዜ ኳስ እና መረብን ማገናኘት ሲችል ኢካይ ጉንዶጋን ቀሪዋን ግብ አስቆጥሯል።
በሌሎች ጨዋታዎች ባየርሊቨርኩሰን ሳልዝበርግን 5ለ0፣ኢንተር ሚላን ሌይፕዚችን 1ለ0 እንዲሁም አታላንታ ከሜዳው ውጪ ያንግቦይስን 6ለ1 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።
በሙሉቀን ባሳ
More Stories
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 6ኛ ዙር መርሐግብር 9 ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ
ሩድ ቫኔስትሮይ የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ሆኖ በይፋ ተሾመ
ሊቨርፑልና ሪያል ማድሪድ በሻምፒዮንስ ሊግ ታላቅ ጨዋታን ዛሬ ምሽት ያካሂዳሉ