አትሌት ቢኒያም መላክ እና ውድነሽ ዓለሙ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የጎዳና ሩጫ ውድድርን አሸነፉ
በሀገር መከላከያ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሀዋሳ ከተማ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ፣ የኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ዋና አዛዥ ሌትናል ጀነራል ሹማ አብደታ እና ሌሎች የሀዋሳ ከተማ እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው ውድድሩ የተካሄደው።
በወንዶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ቢኒያም መላክ ከፀደይ ባንክ ቀዳሚ ሆኖ በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆኗል።
አትሌት ሳሙኤል ፍሬው ከሲዳማ ቡና ሁለተኛ እንዲሁም በግል የተወዳደረው አብዲ ሰላም 3ኛ በመውጣት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በሴቶች ውድድር ደግሞ አትሌት ውድነሽ ዓለሙ ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን በቀዳሚነት አጠናቃለች።
አትሌት ፅጌ ገ/ሰላማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ እንዲሁም ዝማም ባራኪ 3ኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን ቋጭተዋል።
በሁለቱም ፆታ ውድድሩን ከ1ኛ እስከ 5ኛ ለወጡ አትሌቶች ከ500 ሺህ ብር ጀምሮ በየደረጃቸው የገንዘብ ሽልማት ተሸላሚ ይሆናሉ።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።