‎‎የጌዴኦ ዞን አስተዳደር የጌዴኦን ተፈጥሮአዊና ባህላዊ መልክዓ-ምድር በመንከባከብ፣ አካባቢውን ለቱሪስት መስህብና ለኢኮኖሚ እድገት ለማዋል በትኩረት እየሰራ ነው‎‎‎ሀዋሳ፡ መጋቢት 10/2018 (ደሬቴድ)‎የጌዴኦ ዞን አስተዳደር የጌዴኦን ተፈጥሮአዊና ባህላዊ መልክዓ-ምድር በመንከባከብ፣ አካባቢውን ለቱሪስት መስህብና ለኢኮኖሚ እድገት ለማዋል በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ዞኑ ይህን በዩኔስኮ የተመዘገበ ዓለም አቀፍ ቅርስ በዘላቂነት ለመጠበቅ እንዲቻል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
‎
‎
የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር ቅርስ ሰውና ተፈጥሮ ተዋህዶ መኖር  እንደሚችል የሚያሳይ በመሆኑ በዩኔስኮ  መመዝገቡ አንዱ ማሳያ መሆኑን  የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

‎
‎ተፈጥሮ የቸረችውን ውብና ፀጋ  ቅርስ ከአደጋ በመታደግ እና በዘላቂነት በመጠበቅ የቱሪስት መዳረሻና የኢኮኖሚ  ምንጭ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስተዳዳሪው አብራርተዋል ።
‎
‎የዓለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው መልክዓ ምድሩ ባህላዊ እሴቱን ሳይለቅ  ለቀጣዩ ትውልድ  የማሻገር ስራ እየተሠራ  እንደሚሀኝ የገለፁት አስተዳዳሪው ለውጤታማነቱ  ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
‎

‎
‎የዞኑ ቱሪዝም  መምሪያ  ኃላፊው  አቶ እድሉ ታደሰ አባቶች በትውልድ ቅብብሎሽ ጠብቀው ያቆዩትን ቅርስ በመንከባከብና በመጠበቅ ወደ ትውልድ  ለማሻገር ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
‎
‎
‎በመድረኩ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሕይወት ኃይሉ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወይንቱ መልኩ፣ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር)  ጨምሮ የክልል ምክትል የቢሮ ኃላፊዎችና ሌሎችም የሚመለከታቸው  አካላት  ታድመዋል ።
‎
‎
‎ዘጋቢ: ፅጌ  ደምሴ – ከይርጋጨፌ  ጣቢያችን
‎
‎
‎