ስፖርቲንግ ሊዝበን ከአርሰናል ጋር የሚያከናውኑት ጨዋታ ይጠበቃል
የዓላማችን ትልቁ የክለብ እግርኳስ ውድድር የሆነው የአውሮፓ ሻምፒዮንስሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ሲካሄዱ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ስፖርቲንግ ሊዝበንን ይገጥማል።
በሆዜ አልቫሌድ ስታዲየም ምሽት 5 ሰዓት ላይ በያዝነው የውድድር ዓመት በሁሉም ውድድሮች ስኬታማ ጊዜን በማሰለፍ ላይ የሚገኘው ስፖርቲንግ ሊዝበን እና አርሰናል የሚያከናውኑት ጨዋታ ይጠበቃል።
ውጣቱን አሰልጣኝ ሩበን ሌላኛው የእንግሊዝ ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድ አሳልፈው የሰጡት ስፖርቲንጎች አሞሪም ምትክ አድረገው በሾሙት ጆአኦ ፔሬራ እየተመሩ የመጀመሪያ የሻንፒዮንስሊግ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አዲሱ አቀራረብ ሽንፈትን ካላስተናገዱ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ስፖርቲንግ ሊዝበን 10 ነጥቦችን በመያዝ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በፖርቹጋል ከሚገኙ 3 ታላላቅ ክለቦች አንዱ የሆነው ስፖርቲንግ ሊዝበን በያዝነው ዓመት በሁሉም ውድድሮች እስካሁን ሽንፈትን አላስተናገደም።
18 ጨዋታዎችን ያከናወነ ሲሆን 17 ሲያሸንፍ በ1 ጨዋታ አቻ ወቷል።
በሁሉም ውድድሮች ከ5 ጨዋታዎች በኋላ በሊጉ ኖቲንግሃም ፎረስትን በመርታት ወደ አሸናፊነት የተመለሰው አርሰናል በሻምፒዮንስሊጉም ይህንኑ ለማስጠበቅ እያሰበ ይጫወታል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ በሻምፒዮንሊጉ ካከናወናቸው 4 ጨዋታዎች መካከል 2 ያሸነፈ ሲሆን በመጨረሻው ጨዋታ በጣሊያኑ ክለብ 1ለ0 በሆነ ውጤት መረታቱ አይዘነጋም።
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት በሻንፒዮንስሊጉ የተሻለ ደረጃ ላይ መሆን እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።
አሁን ያሉበት ደረጃ ክለቡን እንደማይመጥን የገለፁት አርቴታ በውድድሩ ረጅም ርቀት መጓዝ እንደሚፈልጉም ተናግረዋል።
በአርሰናል በኩል ለረጅም ጊዜ በጡንቻ መሳሳብ ጉዳት ከሜዳ ርቆ የቆየው ስኮትላንዳዊ የክንፍ ተከላካይ ኬየርን ቴርኒይ በቡድኑ ተካቷል፡፡
በሌላ የምሽቱ ተጠባቂ መርሐግብር ምሽት በአሊያንዝ አሬና ከ4 ዓመት በፊት በውውድሩ የፍፃሜ ተፋላሚ የነበሩት ባየርንሙኒክ እና ፒኤስጂ በተመሳሳ ሰዓት ይጫወታሉ።
ሁለቱ ክለቦች በሻምፒዮንስ ሊጉ ለ13ኛ ጊዜ ይገናኛሉ።
ከነዚህ ጨዋታዎች ቀደም ብሎ ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ ስሎቫን ብራቲስላቫ ከኤሲሚላን እንዲሁም የቼክ ሪፐብሊኩ ስፓርታ ፕራግ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ይጫወታሉ፡፡
በተጨማሪም ምሽት 5 ሠዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከሆላንዱ ፌይኖርድ፣ ባርሴሎና ከፈረንሳዩ ብረስት፣ የጀርመኑ ባየርሊቨርኩሰን ከኦስትሪያው ሬድ ቡል ሳልዝበርግ፣ኢንተርሚላን ከአርቢ ሌብዚግ፣ እንዲሁም የሲዊዘርላንዱ ያንግ ቦይስ ከጣሊያኑ አታላንታ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡
በሙሉቀን ባሳ
More Stories
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 6ኛ ዙር መርሐግብር 9 ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ
ሩድ ቫኔስትሮይ የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ሆኖ በይፋ ተሾመ
ሊቨርፑልና ሪያል ማድሪድ በሻምፒዮንስ ሊግ ታላቅ ጨዋታን ዛሬ ምሽት ያካሂዳሉ