ሲዳማ ቡና አቤል ያለውን እና ሱራፌል ዳኛቸውን አስፈረመ
የወቅቱ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ አቤል ያለውን እና አማካዩን ሱራፌል ዳኛቸውን በይፋ አስፈርሟል።
በግብፁ ዜድ እግር ኳስ ቆይታ የነበረው አቤል ያለው ባለፈው ክረምት የቀድሞ ክለቡን ቢቀላቀልም ከቀናት በፊት ከክለቡ ጋር መለያየቱ ይታወሳል።
በዘንድሮው የውድድር ዓመት 15 የሊግ ጨዋታዎችን አከናውኖ 8 ጎሎችን ለቅዱስ ጊዮርጊስ በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ከታምራት እያሱ እና አዲስ ግደይ በጋራ እየመራ ይገኛል።
አሁን ላይ በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመራው ሲዳማ ቡና ቀጣዩ ማረፊያው ሆኗል።
አቤል ያለው ከዚህ ቀደም ከቅዱስ ጊዮርጊስ በተጨማሪ ለአቃቂ ቃሊቲ፣ደደቢት እና ፋሲል ከነማ ተጫውቶ ማሳለፉ አይዘነጋም።
የመሀል ስፍራ ተጫዋቹ ሱራፌል ዳኛቸው ከአሜሪካው ሎዶን ዩናይትድ ጋር ከተለያየ በኋላ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሏል።
ሱራፌል ዳኛቸው በፕሪሚዬር ሊጉ እግር ኳስ መጫወትን በአዳማ ከተማ የጀመረ ሲሆን ወደ ፋሲል ከነማ አምርቶ ከአፄዎቹ ጋር የሊጉን ዋንጫ ማሸነፉ አይዘነጋም።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ