በመንግስት ተደራሽ ያልሆኑ ልማቶችን በጥናትና ምርምር አስደግፎ በመሥራት ረገድ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በመንግስት ተደራሽ ያልሆኑ ልማቶችን በጥናትና ምርምር አስደግፎ በመሥራት ረገድ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የሸኮና አካባቢው ምሁራን ጥናትና ምርምር ማህበር አባላት አስታወቁ።
ማህበሩ በሚያከናውናቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ላይ የተመዘገበውን ውጤት በማጎልበት በትኩረት ሊሠራ እንሚገባም ተገልጿል።
የሸኮና አካባቢው ምሁራን ጥናትና ምርምር ማህበር በመንግስት ተደራሽ ያልሆኑ የተለያዩ ልማቶችን በጥናትና ምርምር አስደግፎ በመሥራት የተጀመረው ጥረት ተጠናክርው ሊቀጥል እንደሚገባ ያነጋገርናቸው የማህበሩ አበላት ተናገረዋል።
ማህበሩ የተዛቡ አመለካከቶችና የፀጥታ መደፈረስን ምክንያት በማደረግ ህብረተሰቡን ሲያውኩ የነበሩትን በመምከር የተለያዩ ጥናትና ምርምርን በመስራት ለውጥ ማምጣት መቻሉንም የማህበሩ የበላይ ጠባቂና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታና የማህበሩ አባልና የቤንች ሸኮ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ማርቆስ ጎቢ ገልፀዋል።
በትምህርት፣ በጤና በግብርና እንዲሁም በተለያዩ መሠረተ ልማቶች ላይ እየተሳተፈ ከመሆኑም በላይ፥ በቀጣይ በሚያከናውናቸው ዘረፈ ብዙ የልማት ተግባራት ዙሪያ እንደመንግስት ከማህበሩ ጎን በመሆን እንደሚደገፉ በሰጡት አስተያየት አብራርተዋል።
የማህበሩ ዓለማ በብሄረሰቡ ባህል ታሪክና ቅርስ ላይ መሠረታዊ የሆኑ ችግሮችን ሊፈታ የሚችል ሀሳብን በማዋጣት በልማት፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በፖለቲካ ላይ ከመሥራትም ባለፈ ለማህበሩ ቅርንጫፍ ጽፈት ቤት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረጉም የየኪ ወርዳ ዋና አስተዳደር አቶ ዳዊት ተሰማና የቢፍቱ ከተማ አስተዳደር አቶ ኦሚስ ካስክራ ተናገረዋል።
በመንግስት ያልተሟሉ ክፍተቶችን በመድፈን ረገድ ሁሉም በተሰማራበት የሙያ ዘረፍ የድርሻውን ሊያበረክት እንደሚገባም የማህበሩ አባልና የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንት አቶ ብንያም ባቡ ገልፀዋል።
ቀደም ሲል በማህበሩ ላይ የነበረው ግንዛቤ በፖለቲካ አደረጃጀት ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ይታሰብ እንደነበረና በአሁን ሰዓት ያልተከናወኑ የተለያዩ የልማት ተግባራትን ለይቶ የሚፈፅም በመሆኑ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንደሚያደረጉም ከማህበሩ አባላት መካከል አቶ ማቴዎስ እንግሊዝ አቶ ከድር ይማም እና ወይዘሮ ተስፋነሽ ወዳጆ አሰረደተዋል።
በሸኮ ባህላዊ የዘመን መለወጫ “ቲካሻ ቤንጊ” በዓል ላይ ጥናትና ምርምር እየሰራ ያለው በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ አማረ ፋንታሁን በበኩላቸው ማህበሩ በተጨባጭ የሚታዩ ተግባራትን ማከናወኑን መመለከታቸውን ገልፀዋል።
ማህበሩ በሚያከናውናቸው በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና በፖለቲካ ዘረፍ ላይ ያስመዘገበውን ውጤት በማጎልበት በአባላት ማፍራት በኩል የሚስተዋለውን ዕጥረት በመቀረፍ ረገድ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባም አስተያየት ሰጪዎች ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎችን በማስፋፋት የእርባታ ስራውን ምርታማነት የማሳደግና የዘርፉን ተጠቃሚነት ለማጎልበት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አፈር አልባ የመኖ አመራረት ዘዴን አስተዋወቀ
በርካቶችን ከድካም የሚታደግ የፈጠራ ውጤት