በክልሉ የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ እንደሚሠራ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ

በክልሉ የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ እንደሚሠራ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ

አሲዳማ አፈርን በኖራ በማከም የስንዴ ምርትን በኩታገጠም አመራረት ዘዴ የዘሩ የደቡብ አሪ ወረዳ አርሶአደሮች ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ በሰፊው እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል እና የግብዓት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግዳልቅ አልቅሚ ገልፀዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስትቲዩት የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ተክሌ ዮሴፍ(ዶ/ር) እንደገለፁት፤ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የምርምር ሥራዎችን በማፍለቅ፣ በማስተዋወቅና በማላመድ እየተሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የአሪ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አፌዶ ወርቁ፤ በዞኑ በኩታ ገጠም ለምቶ የደረሰውን የስንዴ ምርት በሚሰበሰብበት ወቅት ባስተላለፉት መልክት፤ መንግስት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና ምርታማነትን ለመጨመር በትኩረት እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል።

የአሪ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጉራልቅ ይዥማልቅ እንዳስረዱት፤ ከውጪ የሚገባውን የኢንዱስትሪ ምርት ለመተካትና ከተረጂነት ለመውጣት በዞኑ ከ160 ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ምርት መሸፈኑን ገልፀዋል።

በዞኑ ደቡብ አሪ ወረዳ አሲዳማ አፈርን በኖራ በማከም የሰብል ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የተሠራው ሥራ ውጤት ማምጣቱን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገብሬ ባይስጅና የግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ደይዳቆ በጋራ ገልፀው፤ በወረዳው በሁሉም ሰብል አይነት በሄክታር የተሻለ ምርት መኖሩን አብራርተዋል።

የመሬቱን ለምነት ለመጨመር በኖራ በማከምና ከግብርና ባለሙያዎች ያገኙትን ምክረሀሳብ በተግባር ላይ በማዋል የተሻለ ምርት ማግኘታቸውን ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን