አሰልጣኞች ወቅቱ የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲላበሱ እየተሠራ መሆኑ ተጠቆመ

አሰልጣኞች ወቅቱ የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲላበሱ እየተሠራ መሆኑ ተጠቆመ

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ቃል ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች እና ከጋምቤላ ክልሎች የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለተዉጣጡ አሰልጣኞች በቴፒ ከተማ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።

በሥልጠናዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አብይ አንደሞ ፤ ይህ ስልጠና በህዳሴዉ ግብድ ምረቃ ማግስት የሚደረግ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

መንግስት ለዘርፉ በሰጠዉ ልዩ ትኩረት በትምህርትና ስልጠና ላይ በተደረገዉ ሪፎርም በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ላይ ዉጤቶች እየታዩ እንዳሉ ጠቁመዉ፤ ስልጠናው ለ693 አሰልጣኞች ለተከታታይ 12 ቀናት ይሰጣል ብለዋል፡፡

የቴፒ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መልካሙ አየለ በበኩላቸው፤ አሰልጣኞች በየጊዜዉ ከቴክኖሎጂዉ ጋር አብረው እንዲጓዙ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ማስፈለጉን ተናግረዋል።

ሰልጣኞችም ስልጠናዉን በአግባቡ በመከታተል ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ጌትነት ገረመዉ – ከማሻ ጣቢያችን