ከ360 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ የላብራቶሪ ዕቃዎች ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጋቸው ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 09/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የሳውላ ካምፓስ ከ360 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ የላቮራቶሪ ዕቃዎችን ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጋቸው ተመላከተ።
በካምፓሱ የትምህርት ጥራት ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሳውላ ካምፓስ ኃላፊ አቶ ገብረመድህን ጫመኖ እንደገለጹት፥ ካምፓሱ በሁለት ኮሌጆችና በአንድ የትምህርት ክፍል ከ30 በላይ የትምህርት ፕሮግራም በመጀመሪያና በሁለተኛ ድግሪ በማስተማር ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ካምፓሱ በቴክኖሎጁ ዘርፍ የሚታይበትን የቁሳቁስ ዕጥረት ለመቅረፍ ከ360 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ የላራብራቶሪ ዕቃዎች ለተማሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል።
ያደጉና የበለጸጉ ሀገራት መነሻቸው በትምህርት ዘርፉ ላይ ትኩረት ሰጥተው በመስራታቸው መሆኑን ያነሱት አቶ ገብረመድህን፥ በካምፓሱ የላብራቶሪ የቤተ-መጽሐፍትና የኢንተርኔት ክፍሎች ጥራትና አገልግሎት አሰጣጥ ዘመኑን በሚመጥን ደረጃ የውስጥ አደረጃጀቱን በማጠናከር ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ዩኒቨርሲቲው ካሰለጠናቸው ተማሪዎች በትላልቅ አገራዊ ፕሮጀክቶች የሚቀጠሩ ተመራቂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።
መምህር ደረስ ዱማዬ እና መምህር መሪሁን ታፈሰ በሰጡት አስተያዬት ተማሪዎች ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ዘርፍ በዲጅታል የትምህርት አሰጣጥ ላይ ማተኮራቸውን አስረድተዋል።
ካነጋገርናቸው የካምፓሱ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ቢንያም ዳኛቸው እና ተማሪ ጽዮን ታምራት በሰጡት አስተያየት በትምህርታቸው ውጤታማ ለመሆን የጊዜ አጠቃቀማቸውን በፕሮግራም በማድረግና ትምህርታቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚፈጥሩ ድርጊቶች ለመታቀብ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል::
ተማሪ ብረሃን ገብሬ እና ተማሪ ኤሊያስ ሽፈራው በበኩላቸው የቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸውን በማሻሻል ተመርቀው ሲወጡ ስራ ፈጣሪ ዜጋ ለመሆን ከወዲሁ ራሳቸውን እያዘጋጁ ስለመሆናቸው አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
የሀለባ ዞን ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ቢልዮን 293 ሚልዮን ብር ባለይ በጀት አጸደቀ
መስራት እየቻሉ የገንዘብ እጥረት የገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግሮች ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ቀላል አለመሆኑ ተገለጸ
በስልጤ ልማት ማህበር ለ3ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር የተሰበሰቡ የአካባቢው ተወላጆች በዞኑ በሚገኙ የላንፉሮ ወረዳና ጦራ ከተማ አስተዳደር ችግኞችን ተክለዋል ።