ከተለያዩ ሀገር አቀፍ የሚዲያ ተቋማት የተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች በቡርጂ ዞን በክላስተር እየለማ ያለውን ጤፍ ጎበኙ
ለ19ኛ ጊዜ በደቡብ የኢትዮጵያ ክልል የሚከበረውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል አከባበር አስመልክቶ ከተለያዩ ሀገር አቀፍ የሚዲያ ተቋማት የተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን በቡርጂ ዞን በክላስተር እየለማ ያለውን የጤፍ ምርት ጎብኝተዋል።
ቡድኑ ወደ ቡርጂ ሲገባ የዞኑ እና የሶያማ ዙሪያ ወረዳ አመራሮች አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በሶያማ ዙሪያ ወረዳ ነደሌ ቀበሌ የሚገኘውን የክላስተር ጤፍ ሰብል ነው የጎበኙት።
የጉብኝቱ አላማም በደቡብ ክልል በሚገኙ ዞኖች ያለውን እምቅ ሀብት ለሀገር ብሎም ለአለም ማስተዋወቅ ሲሆን ፣በቡርጂ ዞንም በጤፍ ምርት በቂ ምርት እንዳለ ለማየት ተችሏል።
የሚድያ አባላቱ ባዩት የጤፍ ምርት እጅግ መደመማቸውን የገለፁ ሲሆን ኢትዮጵያ በምግብ ሰብል እራሷን ለመቻል እያደረገችው ያለውን ጥረት ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል።
የጉብኝቱ አስተባባሪ የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም ገነሞ የክልል እና ፌደረሽን ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ የሚድያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ።
ዘጋቢ ፡ ወርቅአገኘሁ ወልደየስ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በ2016 ዓመተ ምህረት የምርት ዘመን የስንዴ ምርት በምን ያህል ከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ያውቁ ይሆን?
በዓሉን ለማክበር የሚመጡ እንግዶች ደህንነታቸው ተጠብቆ በቆይታቸው ተደስተው እንዲመለሱ በትራንስፖርቱ ዘርፍ በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ
ከ148ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ እንደሚለማ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ