‎ዞኑ በግማሽ ዓመቱ  1 ሺህ 3 መቶ 25 ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ አቀረበ

‎ዞኑ በግማሽ ዓመቱ  1 ሺህ 3 መቶ 25 ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ አቀረበ

‎ሀዋሳ፣ መጋቢት 08/2018 (ደሬቴድ) በኮሬ ዞን 1 ሺህ 3 መቶ 25 ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ የግማሽ ዓመት አፈጻጸሙን መቶ በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ተገልጿል፡፡

‎‎የኮሬ ዞን ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጃሌ  በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ 2 ሺህ 9 መቶ 30 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እንደነበር ገልፀው በግማሽ ዓመት አፈጻጸም 1ሺህ  3 መቶ 25 ነጥብ 4 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡
‎
‎በዞኑ ከ20 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በቡና ለመሸፈን ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝም ኃላፊው ገልፀዋል፡፡‎
‎
‎አክለውም በዞኑ የቡና ማሣ ሽፋን ከ19 ሺህ  6 መቶ 79 ሄክታር በላይ መሆኑን ገልፀው ከ2 ሚሊዮን 9 መቶ ሺህ በላይ አዲስ  የቡና ችግኞችን ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን አመልክተዋል፡፡
‎

‎
‎ለቡና እንክብካቤ ከማድረግ፣ ያረጁ ቡናዎችን በአዲስ  ከመተካት፣ በኩታ-ገጠም ከመትከልና በጥራት ከማምረት አኳያ ጉድለቶች እንደሚታዩ የገለፁት ኃላፊው እኚህን ችግሮች  ለመቅረፍበ ትኩረት እየሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል ።
‎
‎የኮሬ ቡና በዓለም አቀፍ ገበያ የሚፈለግ የቡና ዝርያ በመሆኑ  ለዓለም ገበያ በሚመጥን መልኩ በጥራት ማምረት አንደሚገባ  ገልጸዋል።
‎
‎
‎ዘጋቢ ፦ ባዩሽ ኢሳያስ- ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
‎